ጥር ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
==============
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል በ22 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የእንጀራ ማምረቻ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተመረቀ። በዕለቱ በመርሐ ግብሩ ብብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕርዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የእንጀራ ማምረቻው በሒደት ከስድስት ሺህ እስከ አስር ሺህ እንጀራ የሚያመርት መሆኑ ተገልጽዋል።
በተያያዘ በዕለቱ ካቴድራሉ የሚያሠራው ኮምፕሬሲቭ ሆስፒታል በቅዱስነታቸው የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።