ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠየቀ።
ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም
=================
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””””””””
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የኅትመትና ሚዲያ ዋና ክፍል ከአህጉረ ስብከት የሚደርሱትን ወቅታዊ መረጃዎችና ዜናዎችን በማስተላለፍ የመረጃ ፍሰቱን የተቀላጠፈ ማድረግ ይቻል ዘንድ”ድምጸ ተዋሕዶ” የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ በመክፈት ወቅታዊ የአህጉረ ስብከት መረጃውችን ማሰራጨት ጀምሯል።
ይህንን መሰረት በማድረግም ዋና ክፍሉ ባስተላለፈው መልዕክት አዲስ በተከፈተው የፌስቡክ ገጽ የሚተላለፉ ወቅታዊ መረጃዎች ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን በፍጥነት እንዲደርሱና ወቅታዊ የአህጉረ
ስብከት መረጃዎችና ዜናዎችን ከአንድ ቋት ማግኘት የሚቻልበትን እድል ለመፍጠር አዲስ የፌስቡክ አካውንት መከፈቱን ጠቅሶ ይህንኑ የፌስቡክ አካውንት ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ወገኖቻችን በተገቢው ሁኔታ እንዲሰራጭ በማድረግ ዋና ክፍሉ አህጉረ ስብከት ተኮር የሆኑ መረጃዎችን በወቅቱ ለማዳረስ እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።በማለት መልዕክቱን አጠቃሏል።