መስከረም 1/2017 ዓ/ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በዕለቱ በዐውደ ምህረት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰ/ት/ት ቤት መዘምራን ያሬዳዊ ወረብ ቀርቧል። በወረዳው ዋና ሥር አስኪያጅ በላዕከ ወንጌል ደግፌ ባንቡራ #”ዓመታትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ” በሚል ርእስ ተነስተው ዛሬ ዓመተ ምሕረት ብለን ስንቆጥር ዘመን የማይቆጠርለት አምላክ ዘመን ተቆጥሮለት ዓመተ ፍዳን አልፈን ዓመተ ምህረት ብለን እንድንጠራና በምህረት ዓመት ውስጥ እንድንኖር አደረገን።

ለዚህ ደግሞ የእኛ ምንም አይነት አስተዋጽኦ የለበትም የእርሱ ቸርነት እንጂ ያ ባይሆን ኖሮ እንደ ምድራዊ ባለ ስልጣናት በር ላይ ተፈትሸን እንድንገባ ቢደረግ ወደ ዚህ ግቢ ማንም መግባት ባልቻለ ነበር? የባለ ስልጣናትን ቤት የሚጠብቁ ለዚህ የተመደቡ ጠባቂዎች አሉ የእግዚአብሔርን ቤት ደግሞ የሚጠብቁ መላእክት ናቸው ግን አንፈተሽም ለምን ቸር ስለሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ በሰጠን እድሜ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ አስተምረዋል።

በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ክፍለ ዮሐንስ አባታዊ መልእክት አስተላልፈው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት