መስከረም 14/2017 ዓ/ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በውይይቱ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ሞላልኝ መርጊያ፣የሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ ዋና ሥራ አስኪያጅ ላዕከ ወንጌል ደግፌ ባንቡራ፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች የመስቀልና የጥምቀት በዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች የተገኙ ሲሆን የበዓሉን ዝግጅት አስመልክቶ የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ መጋቤ ልዑካን አንዳርጋቸው ሙሉጌታ ገለጻ ካደረጉ በኋላ ብፁዕ አባታችን አቡነ ዮሴፍ በየአንዳንዱ ክፍል ላይ ዝርዝር እንዲቀርብ ዕድል ሰጥተው ሁሉም ክፍሎቹ በቅደም ተከተል አቅርበዋል።
1ኛ/ ጸጥታ ክፍል
2ኛ/ መድረክ ዝግጅትና ድምፅ
3ኛ/ የደመራ ችቦ ዝግጅት ክፍል
4ኛ/የሊቃውንት ክፍል
5ኛ/ የሰ/ት/ት ቤት ክፍል
6ኛ/ ሚዲያ ክፍል ከላይ የተዘረዘሩት ክፍሎች ያደረጉትን ዝግጅት ካቀረቡ በኋላ የጉባኤው አባላት የተለያዩ ሀሳቦች አንስተዋል።
በመቀጠል የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ሞላልኝ መርጊያ የቀረበው ሀሳብ ጥሩ ነው እንደ አጠቃላይ ግን ዝግጅቱ ያማረ እንዲሆን ሁላችሁም ጠንክራችሁ መሥራት አለባችሁ በማለት መመሪያ ተሰጥተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ይህን በዓል ስናከብር ሁሉም ክፍሎች በዚህ ልክ መዘጋጀታችሁ መልካም ነው። ምክንያቱም ይህን በዓል የምናከብረው ሃይማኖታዊ ስለ ሆነ እንጂ ከባህል አንጻር አይደለም ስለዚህ ዝግጅቱ መልካም ነው። በሌላ መንገድ ከጸጥታ አንጻር በትኩረት መሠራት አለበት።

በዓላችን ሲመጣ የሥጋት ምንጭ ሳይሆን የሰላም ምንጭ ሆኖ መጣልን መባል አለበት ለዚህ ደግሞ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል በአጠቃላይ ዝግጅታችሁ በጣም ጥሩ ነው ነገር ግን በተዘጋጀነው ልክ ሲፈጸም ስኬቱ የሚያምር ስለ ሆነ ለዚህ እስከ መጨረሻው ጠንክራችሁ መሥራት እንድትችሉ አደራ እላለሁ በማለት አባታዊ መመሪያ አስተላልፈው በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ውይይቱ ተጠናቅቋል።

መረጃው የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት