ጥር ፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በመንፈሳዊ ዘርፍ የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅና የዐቢይ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ በተገኙበት በጠቅላይ ቤተክህነት የተቋቋመው የጥምቀት በዓል ዐቢይ ኮሚቴ ሲያከናውናቸው የሰነበተውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች  በዛሬው ዕለት ገምገማ ተደርጓል።

በግምገማው በንዑሳን ኮሚቴዎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በአፈጻጸም የተስተዋሉ ክፍተቶች በአስቸኳይ ተሟልተው እንዲፈጸሙ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በማዕከል በጃን ሜዳ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች  በነገው ዕለት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በተገኙበት ጉብኝት የሚደረግ ሲሆን  በዚሁ የግምገማ መርሐ ግብር ላይም ብፁዕነታቸው በሰጡት መመሪያ በሁሉም ንዑሳን ኮሚቴዎች የተከናወኑት ሥራዎች ምስጋና የሚገባቸው መሆኑን ጠቅሰው ቀሪ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሁሉ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲከናወኑና የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረግ ግንኙነት መፍትሔ እንዲሰጥባቸው አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።