ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያነት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
+++++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ለ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል። ማብራሪያውን የሰጡት የአገር አቀፍ ሰ/ት/ቤት አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው እንደተናገሩት የሰ/ት/ቤች ሥርዓተ ትምህርትን ለመቅረጽ እጅግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።

አሁን ተቀርጾ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚጠበቀው ሥርዓተ ትምህርት 6 ዋና ርእሶች እና አንድ ደጋፊ ርእስ ያለው ሲሆን ለዘንድሮው ዓመት ትግበራ እንዲሆን 42 መጽሐፍት ታትመው እና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ዝግጁ ሆኗል።

አቅራቢው በተጨማሪ እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ አሁን ያለው ትውልድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተረድቶ መንፈሳዊ ወጣት እንዲሆን የሚያስችል ዕውቀትን የያዘ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት አሁን ያለውን ትውልድ ለማዳን ሰ/ት/ቤትን ማጠናከር የግድ ይለናል ብለዋል።

በተጨማሪም በሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል።