ጥር ፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
++++++++++++++++
ኢሉ አባቦራ-ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””””

ማኅበረ ቅዱሳን ጎሬ ወረዳ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል ያሠለጠናቸውን 22 ካህናትን የኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የመቱ ፈለገ ሕይወት መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)፣ የኢሉ አባ ቦር ሀገረ ስብከት የመምርያ ኃላፊዎች ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መቱ ማዕከል ፣ ተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በኖኖ ሳርዶ ማርያም በአቡነ ሚካኤል ካልዕ ስም በተገነባው አብነት ትምህርት ቤት ውስጥ አስመርቋል።

ካህናቱ በቆይታቸው ሰዓታት ፣ ኪዳን ፣ ሊጦንና ቅዳሴ በግዕዝና በዕዝል ተምረው ለአገልግሎት እንዲዘጋጁ የተደረገ ሲሆን ቀድሰው ከወጡ በኋላ ወንጌል እንዲያስተምሩ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችንም መማራቸው ተጠቁሟል።

ብፁዕነታቸው ሀገረ ስብከቱ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ለማስከፈት እየሠሩ መሆኑን በመግለጽ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

የጎሬ ወረዳ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ምትኩ ተፈሪ እንዳመለከቱት ለሥልጠናው ሀገር ውስጥና ሀገር ውጭ ከሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በማሰባሰብ ከ 750,000 ብር በላይ ወጪ መደረጉን በመግለጽ የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ለማስከፈት በ 2015 ዓ.ም ዕቅድ ነድፎ እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

©ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ነው