ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤላይ ያቀረበው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚከተለው ነው።

ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
****
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ማኅበረ ቅዱሳን በ፳፻፲፭ ዓ.ም ካከናወናቸው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ውስጥ የሚከተሉት ዐበይት ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

1. የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት
* ከ300 ሺ በላይ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በሀገር ውስጥ በ467 እና በውጭ ሀገር በ18 ግቢ ጉባኤያት ውስጥ በተለያዩ ቋንቋዎች እያስተማረ ይገኛል፡፡ በ35 ማእከላት 7966 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ከኮርስ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የአብነት ትምህርት የተማሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ትምህርታቸውን ተምረው ለክህነት የደረሱ 195 ተማሪዎች ክህነት እንዲቀበሉ ተደርጓል፣
* በማእከላት አስተባባሪነት ከየግቢ ጉባኤያቱ የአገልግሎት ክፍሎች ለ2363 መሪ ተማሪዎችን በደረጃ 1 ሥልጠና ተሰጥቷል፣ የደረጃ 2 አመራር ሥልጠና ከማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
* የውጭ ዜጎችን እና የኢትዮጵያውያንና ዲዮስጶራዎች መሠረት ያደረጉ 4 ቨርቹዋል ግቢ ጉባኤያት ተቋቁሟል፡፡
*ለአይነ ስውራን የሚሆኑ 2 የግቢ ጉባኤያት የኮርስ መጻሕፍት ማስተማርያዎች በድምጽ ተዘጋጅተው ለማእከላት ተልከዋል፡፡
* ነባር የግቢ ጉባኤያት ኮርስ መጻሕፍት በማጣቀሻነት ሊያገለግሉ በሚችሉበት መልኩ እንዲሁም 5 የግቢ ጉባኤያት የኮርስ መጻሕፍት በአማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች በድጋሜ ታትመው በስርጭት ላይ ይገኛሉ፡፡

2. በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት የተሠሩ
* በተለያዩ ቋንቋዎች በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰማሩ አገልጋዮች 865 ሰባክያነ ወንጌል፣ 218 የጎሳ መሪዎች እና 231 ባለሙያዎች እና በውጭ ሀገር ለሚሰማሩ 130 አገልጋዮች የሰባኬ ወንጌልነት ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
* ካህናት አባቶችን በስብከተ ወንጌል ለማሰማራት 1983 ካህናት በክብረ ክህነት እና መምህረ ንስሐነት ሥልጠና ተሰጥቷል፣ ለሥልጠናዎች ማስፈጸሚያም 3,807,749.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
* በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰማሩ 204 አገልጋዮች 3,152,400.00 ብር ወጪ በማድረግ ወርኃዊ ደመወዝ በመክፍል ድጋፍና ክትትል ሲደረግ፣ አዳዲስ አማንያንን ለማጠመቅና ለማጽናት 9,234 ትምህርታዊ ጉባኤያት በተለያዩ አካባቢዎች ተከናውነዋል፡፡
*የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ቋንቋዎች 188 ትምህርታዊ ጉባኤያት ሲከናወኑ፣ ለጉባኤያቱ ማስፈጸሚያ 3,760,000.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
*በተለያዩ ቋንቋዎች (በአሪኛ፣ ማሌኛ፣ ጋሞኛ፣ ኮንሶኛ፣ ወላይትኛ፣ ዳውሮኛ፣ ሐዲይሳ፣ ጌዲዮፋ፣ ሲዳምኛ፣ ከፍኛ፣ ቤንችኛ፣ ኦሮምኛ፣ ከምባትኛ፣ ትግርኛ፣) ትምህርቶችን በማዘጋጀት፣ በመተርጎምና የአርትኦት ሥራ በመሥራት ለሚሳተፉ 32 አገልጋዮች ሥልጠና ተሰቷል፡፡ ለዚህም 265,000.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡ ከላይ ባሉት ቋንቋዎች የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ተዘጋጅቶ ለምእመናን ተሰራጭቷል፡፡
* በተለያዩ አካባቢዎች ተደራሽ በተደረገው ሐዋርያዊ አገልግሎት 36,635 አዳዲስ አማንያን በሀገር ቤት 48 አዳዲስ አማንያን ደግሞ በውጭ ሀገር ተምረው አምነው በመጠመቅ የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል፡፡ ለሥርዓተ ጥምቀቱ ማስፈጸሚያም 4,501,144.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
* ከአዳዲስ አማንያን መካከል አገልጋዮችን ለማፍራት 231 የአዳዲስ ልጆች የአብነት ትምህርት ባሉበት እየተማሩ እና አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን ዘጠኝ ልጆች ደግሞ የትምህርት እድል ተሰጥቶአቸው በፍኖተ ሰላም አቡነ ቶማስ መታሰቢያ ቤተ ጉባኤ በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም 277,748.00 ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡
* ለአዳዲስ አማንያን መገልገያ የሚሆኑ በከምባታ ጠምባሮ ሀላባ ሀገረ ስብከት ሁለት (2)፣ በወላይታ ሀገረ ስብከት ሁለት (2)፣ በጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት አንድ (1)፣ በቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሦስት (3)፣ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሦስት (3) እና በካፋ ሀገረ ስብከት ሁለት (2) አብያተ ክርስቲያናት የታነጹ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል ሰባት (7) አብያተ ክርስቲያናት ተመርቀው አገልግሎት ጀምረዋል፡፡ ሁለት (2) አብያተ ክርስቲያናት ሥራቸው ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጁ ሆነዋል፡፡ ሌሎች አራት አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ አብያተ ክርስቲያናቱን ለማሳነጽ 27,790,019.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
* ለአዳዲስ አማንያን መሰብሰቢያና ቅድመ እና ድኅረ ጥምቀት ማስተማሪያ የሚሆኑ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሦስት (3)፣ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት አንድ (1) እንዲሁም በወላይታ ሀገረ ስብከት አንድ (1) በአጠቃላይ አምስት (5) የስብከት ኬላ አዳራሾች ተሰርተዋል፡፡ ለዚህም 4,120,888.00 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
* ስብከተ ወንጌልን በተለያየ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ በርቀት ትምህርት 1155 በሞጁል እና 91 በኢለርኒንግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ፣ ለዚህም 652,232.00 ብር ወጪ ተደርጎ፡፡

3. በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት በማኅበራዊ ዘርፍ
* በ4 ሀገረ ስብከቶች ማለትም በሰሜን ምዕራብ ሸዋ /ሰላሌ ፍቼ፣ በምዕራብ ሸዋ አምቦ፣ ሰሜን ሸዋ አጣየና ሸዋሮቢት፣ እንዲሁም ዋግኽምራ ለሚገኙ 1015 ለሚሆኑ ተማሪዎች 809,395.00 ብር በላይ ወጭ የሆነበት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
* በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ጉዳት ለደረሰባቸው በሻሸመኔ ከተማ ለሚገኙ ያክል የሰማዕታት ቤተሰቦችና በአዲስ አበባ ወለቴ ለሚገኙ ተጎጅዎች በድምሩ 353,000.00 ብር የሕክምና ድጋፎች ተደርጓል፣
* ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 10 ገዳማት ለሚገኙ መነኮሳት፣ አብነት ተማሪዎችና አገልጋዮች 820,000.00 የፈጀ አስቸኳይ ድጋፍ ተደርጓል።
* በቦረና ዞን በያቤሎ ወረዳ ዙሪያ ተፈናቅለው ለሚገኙ ተጎጅዎች 397,100.00 ብር ወጭ አስቸኳይ ድጋፍ ተደርጓል።
*በጎንደር አዘዞ ቀበሮ ሜዳ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ500,000.00 በላይ ወጭ ተደርጎ የአስቸኳይ ምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
* በሃይማኖት ጥቃትና መፈናቀል የከፍ ችግር ለደረሰባች ካህናትና አገልጋዮች 266,675.00 ብር ድጋፍ ተደርጓል።
* በአጠቃላይ ለአስቸኳይ የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶች ትግበራ 3,448,045.00 በላይ ወጭ ተደርጓል።
*ሙያዊ ግምታቸው 9,710,600.00 ሚሊዮን ብር የሆኑ 42 ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው የቤተ ክርስቲያን እና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ሕንጻ ዲዛይኖች እና 2.3 ሚሊዮን ብር የሆኑ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች በነጻ ተሠርተው ተሰጥተዋል፤ 20 የሚሆኑ የምሕንድስና መስክ ሱበርቪዥን አገልግሎቶች ተሰጠዋል። በዚህም 4.5 ሚሊዮን ብር ከወጭ ማዳን ተችሏል።

4. መዝሙርና ሥነ ጥበባት ሥራዎችን በተመለከተ
*አዳዲስ በአማርኛ፣ በትግርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች የምስል ወድምጽ 3 የበገና መዝሙራት አልበሞች ታትመዋል፣

* በአማርኛ ቋንቋ ቁጥር ፯ እና በኦሮምኛ ቋንቋ ቁጥር ፪ የምስል ወድምጽ መዝሙራት አልበሞች ታትመዋል፣
*በአርባ ምንጭ ማእከል በ፭ ቋንቋዎች እንዲሁም በሚዛን ማእከል በ፭ ቋንቋዎች መዝሙራት የአርትኦት ሥራቸውን ተጠናቅቀው ለኅትመት ዝግጁ ሆነዋል፣
* በጋሞኛ 48 መዝሙራት፣ በኮንሶኛ 56 መዝሙራትና በኧሊኛ 58 መዝሙራት የቀረጻ ሥራ ተከናውኗል።
* “ቅዱስ ያሬድና ሥራዎቹ፣ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ለጠንካራ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ያላቸውን ሚና” የሚያሳይ ከ3000 በላይ ምእመናን የተሳተፉበት ከግንቦት 10 – 13 ቀን 2015 ዓ.ም የቆየ ዝክረ ቅዱስ ያሬድ ዐውደ ርእይ ተከናውኗል፤

5. ቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ት/ቤቶችን በተመለከተ
*በ165 አብነት ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 229 መምህራን እና 1949 ደቀመዛሙርት ድጎማ 5,544,500.00 ድጋፍ ተደርጓል።
* በአዲስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ የትምህርት ዕድል መርሐ ግብር ከዘመናዊ ወደ አብነት ለ77 ተማሪዎች፣ በመንፈሳዊ ኮሌጅ 11 ደቀመዛሙርት፣ ከአብነት ወደ ዘመናዊ ለ15 የአብነት መምህራን በድምሩ ለ103 የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነጻ ትምህርት ዕድል መርሐ ግብር ተጠቃሚዎች በመማር ላይ የሚገኙ ሲሆን 1,271,600.00 ወጪ ተደርጓል።
* ከደቡብ፣ ከምእራብ እና ከምሥራቅ ከሚገኙና የአገልጋዮች እጥረት ካለባቸው አካባቢዎች 83 ዲያቆናት ወደ ነባር አብነት ት/ቤቶች ሄደዉ ተጨማሪ የአብነት ትምህርት እንዲማሩ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷል፤ ለዚህም 448,200.00 ብር ወጪ ተደርጓል።
* በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው በሰሜን ወሎ እና በዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ 12 ገዳማት እና 13 የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ለጣና ቂርቆስ አራቱ የመጽሐፍ ጉባኤ አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት 1,610,000.00 ብር የቀለብ ድጋፍ ተደርጓል።
* በሶማሌ ሀገር ስብከት የቅድስት አርሴማ ገዳም አዳሪ የአብነት ት/ቤት፣ በአፋር ሀገረ ስብከት የአዋሽ አርባ ደብረ ሓራ ቅ/ሚካኤል ወአቡነ አረጋዊ ገዳም የብፁዕ አቡነ ዮናስ መታሰቢያ አብነት ት/ቤት፣ በአርሲ ሀገረ ስብከት የማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያም ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ገዳም መልእክተ ዮሐንስ አብነት ት/ቤት ተገንብተው ለሀገረ ስብከቶች ርክክብ ተደርጓል፣ ለፕሮጀክቶችም ብር 15,518,741.84 ወጭ ተደርጓል፡፡
* በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም አብነት ት/ቤት የመምህራን ማረፊያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በብር 1,236,386.53 ብር ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፣

ተጨማሪ ዓበይት ተግባራት
* የቤተ ክርስቲያን ሀገራዊ አበርክቶ የሚመለከቱ ከተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ 7 የጥናት መድረኮች እና የምሁራን ውይይት ተካሂደዋል፡፡ 1 ደራጃውን የጠበቀ የጥናት መጽሔት ተዘጋጅቶ ታትሞ ተሰራጭቷል::
*ለቴሌቪዥን ስርጭት በማስፋት እስካሁን ከነበረው 6 ቋንቋዎች በተጨማሪ 1 አዲስ ቋንቋ (በወላይትኛ) በመጨመር የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ሲሆን ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደውን ህገ ወጥ የኤጴስቆጶሳት ሹመት ለምእመናን በቀጥታ ስርጭት ጭምር በማደረስ የቤተ ክርስቲያኗ ድምጽ በመሆን ታሪክ የማይረሳው ውለታ ሠርቷል::
በአጠቃላይ ማኅበሩ በበጀት ዓመቱ የያዛቸውን እቅዶች ለማከናወን ከአባላቱ እና ድጋፍ ከሚያደርጉ ምእመናን ብር 126,944,733.57 ያሰባሰበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር 119,986,278.26 ወጭ የተደረገ ሲሆን ቀሪው ብር 6,958,455.31 ለቀጣይ በጀት ዓመት አሸጋግሯል፡፡ ማኅበሩ በየዓመቱ ያለውን የገንዘብ ወጭ እና ገቢ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር መምሪያ በተወከሉ ኦዲተሮች እና በውጭ ኦዲተር እያስመረመረና ትክክለኛነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

ጥቅምት ፳፻፲፭ ዓ.ም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር