የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት 42ኛ ዓመት የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያስተላለፋት ሙሉ የመክፈቻ መልእክት

October 16, 2023

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

•ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
•ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳስት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
•የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፣
•የየሀገረ ስብከቱ ተወካዮች፣
•የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣
•ከልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የመጣችሁ እንግዶች፣
•በአጠቃላይ በዚህ ዓቢይ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ

እግዚአብሔር አምላካችን ከዓመት ዓመት አድርሶ ይህን የተቀደሰ ቀኖናዊ ጉባኤ ለማካሄድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለሱ እናቀርባለን እናንተንም እንኳን ደኅና መጣችሁ እንላለን፡
“በብዙኅ ሕማም ሀለወነ ንባኣ ለመንግሥተ እግዚአብሔር” ወደ እግዚብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ይገባል (የሐ.ሥራ 14፥22)

ይህ የቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ጠንካራ ጥረትና ጽናት የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያስገነዝብ ገዢ አስተምህሮ ነው ከቅዱስ መጽሐፍም ከታሪክም በትክክል ተመዝግቦ እንደሚገኘው የቤተክርስቲያን ጉዞ ገና ከጅምሩ አንሥቶ በጸዊረ መስቀል የታጀበ ነው

ጸዊረ መስቀል ምንም የመረረ ቢሆንም ተሸንፎ ግን አያውቅም ነገረ መስቀል በአሸናፊነት እንጂ በተሸናፊነት አይታወቅምና ነው ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ መግባት አለብን ሲሉ የመከራ መስቀል ዓጸፋ አሸናፊነትና መዳን መሆኑን ስለሚያውቁ ነው በሀገራችንም ሆነ በመላው ዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖች የተለያዩ ጸዋትወ መከራዎችን በመቀበል የሚገኙት ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ከሐዋርያት ተጋድሎ ባገኙት ውርስ ነው፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

እንደ ዕድል ሆኖ ዘመናችን በመከራ መስቀል የታጀበ ሆኖ ይታያል ብዙ ክርስቲያኖች በአሁኑ ጊዜ በዚህ ፍኖተ መስቀል እያለፉ ነው አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን እየተፈናቀሉ፣ እየተሰደዱና እየተገደሉ ነው ሌላም ጫና ሁሉ እያንገላታቸው ነው ይህ ሁኔታ ሄዶ ሄዶ ሃይማኖቱን የሚያዳክም ነው ሃይማኖቱ ሲደክም ደግሞ ኢትዮጵያዊ ማንነትና ባህል አብሮ ይደበዝዝና አለን ብለን የምንመካበት ዕሤት በሙሉ ነበረ ወደ ማለት ይቀየራል ታሪኩን ሃይማኖቱንና ባህሉን ሥነ ምግባሩንና ትውፊቱን ያጣ ወይም የማያውቅ ትውልድም ይተካና ሁሉም በጨለማና በድንግርግር ይዋጣል

ይህ ዓይነቱ የሃይማኖት የታሪክ የማንነትና ባህል ውድቀት እንዳያጥለቀልቀን ጠንክሮ መስራት ዛሬ ከምንም ጊዜ በላይ ይጠበቅብናል የኛ ዐቅም ከመንፈስ ቅዱስ መንጭቶ በምእመናን ልቡና የሚመላለስ ኃይል ስለሆነ ይህንን ዐቅም ለመጠቀም ከሁሉ በላይ ምእመናንን በእንክብካቤ መያዝ ያስፈልገናል በዘመነ ሰማዕታት ቤተክርስቲያንን በፀዊረ መስቀል ያሻገሯት ካህናትና ምእመናን እንደፈትልና ሰም ተዋሕደው ነው ለምእመናን የምናቀርበው አገልግሎት ሁሉ የምእመኑን ልብ የሚረታና ለሃይማኖቱ በፍጹም ልቡ ታማኝ ሆኖ እንዲቆም የሚያስችል ሊሆን ይገባል፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

ሁላችንም እንደምንገነዘበው አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ በተወሰነ የንዋይ አሰባሰብ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ መለስ ተልእኮ ላይ የሚሠማራ ዓቢይ ተልእኮ ነው በተለይም በምእመናን ህልውናና ደኅንነት ላይ አብዝቶ መስራት ያስፈልጋል ምእመናን ካሉ ሁሉም አለ ምእመናን ከሌሉ ግን ሁሉም የለም ይህንን ሁላችንም በትኲረት ልንገነዘብ ይገባል፡፡
ሌላው ልናልፈው የማንችል ታላቅ ነገር የቤተክርስቲያናችንን አንድነት ነው በቤተክርስቲያን አንድነት እንደዚሁም በሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ይዘቱ ላይ ጥያቄ ያለው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም በዚህም ብዙ ልዩነት አናይም ነገር ግን በአንዳንድ አስተዳደራዊና ዘመን ወለድ ቅሬታዎች አንድነታችን እየተፈተነ ነው ይህ የማንም ስሕተት ሳይሆን በውስጣችን የተፈጠረ ዕንቅፋት ነው
በመሆኑም ይህ እየተፈታተነን የሚገኘው የአንድነት ፈተና በተለመደው የቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ በጥበብና በብልሐት ማረም ግድ ይለናል ቅሬታ ብቻ ሳይሆን የቅሬታ መፍቻም አለና እሱን ተጠቅመን አንድነቱን ማምጣት አለብን ተለያይቶ መኖር ያሳፍራል ያዳክማልም እንጂ በየትኛውም መመዘኛ ብርታት ይሰጣል ተብሎ አይገመትም ስለሆነም ቅሬታን በድርድርና በውይይት በይቅርታና በመተማመን ዘግተን አንድነታችንን ማጽናት አለብን፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

ቤተክርስቲያናችን ወደ ፊት ተራምዳ ታላቁ ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ካደረጋት አንዱ የአሰራር ስልታችን እንደሆነ ማንም አይስተው በመሆኑም ይህንን ዘመኑን የማይዋጅ የአሰራር ስልታችን ለማሻሻል የሚያስችል፣ ሊመራና አቅጣጫ ሊያመላክት የሚችል መሪ ዕቅድ እንዲዘጋጅ በቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑ ይታወቃል በውሳኔው መሠረት የመሪ ዕቅድ ሰነድ ተዘጋጅቶና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ ይሁንታ አግኝቶ በአሁኑ ጊዜ የሥርጸትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ
በመሆኑም መሪ ዕቅዱ፣ አሰራራችንን መልክ በማስያዝ፣ ለውጤት በሚያበቃ አተገባበርና አፈጻጸም በመከተል በመናበብና በመግባባት ልንጠቀምበት ይገባል ሃይማኖትን ከመንካት በቀር ሃይማኖታችንን ለማስጠበቅ የሚያስችለንን የዘመኑ ቴክኖሎጂ (የአሰራር ጥበብና ዘዴ) በሙሉ ተጠቅመን መምራት ጊዜው የሚጠይቀው ቊልፍ ተግባር ነው
ከዚህ ሌላ ትንሽም ሆነ ትልቅ ስራ መስራትና ውጤት ማስመዝገብ የሚቻለው ሰላም ሲኖር ነው ሀገራችንን ጨምሮ በአካባቢያችን የሚገኙ ጎረቤቶች በሰላም እጦት እየተንገላቱ ነው ስለሆነም አሁንም አብዝተን ወደ አምላካችን በመጸለይ፣ ስለ ሰላም ስለ አንድነትና ስለ ወንድማማችነት ፍቅር ደጋግመን ልናስተምርና ልንጮህ ይገባል መንግሥታችንም የአብያተ ሃይማኖት ደኅንነት የካህናትና የምእመናን የመኖር ዋስትና የሁሉም ዜጎች ሰላማዊ ኑሮ በማስፈን ለአካባቢው ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ፣ ሕዝቡም ለዚሀ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ በዚህ አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም
በዚህ ዓለም ዐቀፋዊና ዓመታዊ የቤተክርስቲያናችን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመገኘት ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጣችሁ ሁላችሁም በድጋሚ እንኳን ደኅና መጣችሁ እያልን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 32ኛውን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ፵፪ ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የስተላለፉት መልዕክት። Link to: ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ፵፪ ኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የስተላለፉት መልዕክት። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና... Link to: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤላይ ያቀረበው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚከተለው ነው። Link to: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤላይ ያቀረበው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚከተለው ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በ፵፪ ኛው አጠቃላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top