የካቲት ፳፪ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቐለ አሉላ ኣባነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል ።

በአየር ማረፍያ ሲደርሱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተክህነት ሠራተኞች እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምእመናን አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

የብፁዕነታቸውን እረፍት ተከትሎ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን መቐለ የገቡ ሲሆን በብፁዕነታቸው የሽኝት መርሐ ግብር ላይም የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ማምሻውን ወደ አዲስአበባ ይመለሳሉ።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን።