ከሐምሌ ፲፬-፲፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ ም ለሁለት ቀናት በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የጉባኤ አዳራሽ በሀገረ ስብከትቦቱ የ፲ ዓመት ስልታዊ እቅድ ዙሪያ የተካሄደው የምክክር ጉባኤ መጠናቀቀ።
ከ፳፻፲፮-፳፻፳፭ ለአስር ዓመታት ያገለግላል ተብሎ የታያሰበውንና የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ ችግር ይፈታል ተብሎ የተዘጋጀው ስልያዊ እቅድ በታህሣሥ ወር ፳፻፲፭ ዓ ም በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ መመሪያ ሰጭነት በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በተቋቋመው የስልታዊ እቅድ አዘጋጅ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ በሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ አባላትና ልዩ ልዩ ባለሙያዎች አስተያየት ሲስጥበት መቆየቱ ታውቋል።
ከዚሁም ጋር ከቤተ ክርስቲያኒቱን በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማት እንዲያገለግል ከአዘጋጀችውም መሪ እቅድ ጋር ተገናዝቦና የሀገረ ስብከቱን ውስጣዊና ውጫው ሁኔታ ዳሶ የተዘጋጀ መሆኑ ተብራርቷል።
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣የልማትና እቅድ ክፍል ኃላፊዎች፣የምእመናን ተወካዮች ፣ከሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት፣ከማኅበረ ቅዱሳን፣ከወጣቶች ኅብረት፣የደብረ ማርቆስ ከተማ አጥቢያ አስተዳዳሪዎችና ጥሪ የተደረጋቸው ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በሁለቱ ቀናት የምክክር ጉባኤ ላይ በባለሙያዎች በተዘጋጀውና በአስተዳደር ጉባኤው ይሁንታ ባገኘው ስልታዊ እቅድ ዙሪያ በ፬ ምሑራን ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቡድን ሆነው ውይይት አድርገው የውይይት ውጤታቸውን አቅርበዋል።
የተዘጋጀው ስልታዊ እቅድም የተሰጡ ሀሳቦችን አካቶ የሀገረ ስብከቱ የመጭዎች ፲ ዓመታት እቅድ እንዲሆን በጉባኤው ጸድቋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጉባኤው ተጠናቋል።
መረጃው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው።