ሚያዝያ ፪ቀን ፳፻ ፲ወ ፭ ዓ.ም
*******
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በሱዳን ካርቱም የሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደርና በህዝበ ክርስቲያኑ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት በማስመልከት በዝርዝር አጣርተው የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ የተመደቡት ሦስቱ የቤተክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር ጉባኤ አባላትም ሥራቸውን ለማከናወን ካርቱም ገብተዋል።

ልዑካኑ ካርቱም የገቡት አስተዳደር ጉባኤው ችግሩን በጥልቀት በማጥናትና በዝርዝር በማጣራት ፍትሐዊ የሆነ የውሳኔ ሀሳብ እንዲያቀርቡ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ሲሆን በትላንትናው ዕለት የተከበረውን የሆሳዕና በዓልንም በሱዳን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተገኝተው አክብረዋል።ሰፊ ትምህርተ ወንጌልም ሰጥተዋል።በዛሬው ዕለትም የማጣራት ሥራውን ለማከናወን ባወጡት እቅድ መሰረት ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸው ታውቋል።