ጥቅምት 27/2017 ዓ/ም
+ + +
በበዓሉ ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ አባል፣ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሰሜን አሜሪካ የኮሎራዶና አካባቢው ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ተገኝተዋል። በዕለቱ በዐውደ ምሕረት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰ/ት/ት ቤት መዘምራን በቅደም ተከተል ያሬዳዊ ወረብ ቀርቧል።
በማያያዝ እየተሠራ ስላለው ግዙፍ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በደብሩ አስተዳዳሪ በመልአከ ስብሐት ቀሲስ ኪነ ጥበብ ያለው ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በመቀጠል የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ መልእክት ከአስተላለፉ በኋላ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ትምህተ ወንጌል ተሰጥቷል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የዐውደ ምሕረቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው