የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ጥገና መዘግየት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋትን አስከትሏል ተባለ።

November 7, 2024

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
+ + +

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከጥቅምት 24-27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሐዋርያዊ ጉዞ አድርገዋል። ብፁዕነታቸው የቅዱስ ላሊበላ ደብር የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የእድር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመሪ እቅድ አተገባበር፣ በቅርሱ ጥገናና እንክብካቤ ዙሪያ አወያይተዋል። የቅዱስ ላሊበላ አብያተክርስቲያናት መጠለያ አለመነሣቱና የቅርሱ ጥገና መዘግየት እንዲሁም በአካባቢው የሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ ያስከተለው ንዝረት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን ተሳታፊዎች አንሥተዋል።

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ መ/ር አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ (ቆሞስ) በበኩላቸው አካባቢው የጦርነት ቀጠና ቢሆንም ቤተክርስቲያኗ በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአስተዳደር ዘርፎች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንድታስፋፋ ታልሞ የተዘጋጀውን መሪ እቅድ ለማሳካት ደብሩ የአስተዳደር ደንብና መዋቅር እያጠና መሆኑን አብራርተዋል። በደብሩ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ለማሻሻል የሚያግዝ የአስተዳደር ደንብ በባለሞያዎች እየተዘጋጀ ስለመሆኑም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት የማጠቃለያ አባታዊ መልእክት በፈተናዎች ውስጥ ብንሆንም እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የተዘጋጀውን የሀገረ ስብከት ሥልታዊ እቅድ እስከ አጥቢያ ድረስ ማውረድ ተችሏል ብለዋል። በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ምሁራን የተዘጋጀውን የ10 ዓመት መሪ እቅድ ተገንዝበን መተግበር ከቻልን ኹሉም ጥያቄዎቻችን መልስ ያገኛሉ ብለዋል ።

በቅዱስ ላሊበላ ቅርስ ደኅንነት፣ በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግሥት ስምምነት የተጀመረው የዘላቂ ላሊበላ ቅርስ ጥገና ፕሮጀክት መዘግየት፣ በመዳረሻ ልማትና ማስተዋወቅ ዙሪያ ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫ መቀመጡንም ብፁዕነታቸው ተናግረዋል። ብፁዕነታቸው ለሦስት ቀናት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት፣ በማስተማርና አባታዊ መመሪያ በማስተላለፍ በቅዱስ ላሊበላ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው በሰላም ተመልሰዋል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የመድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያና የጻድቁ አባታችን የመባዓጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የመድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያና የጻድቁ አባታችን የመባዓጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምጥማቅ... Link to: የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዐመታዊ መታሰቢያ በዓል በመላ ኢትዮጵያ በሌዩ ልዩ ሥፍሬዎች ላይ በድምቀት  ተከብሮ ዋለ። Link to: የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዐመታዊ መታሰቢያ በዓል በመላ ኢትዮጵያ በሌዩ ልዩ ሥፍሬዎች ላይ በድምቀት  ተከብሮ ዋለ። የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዐመታዊ መታሰቢያ በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top