በቀድሞ ስማቸው እነ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል።
የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ/ም