የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

አሥሩን ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመተግበር እነ አቡነ ሳዊሮስ ተስማሙ።ወቅታዊ መግለጫ

February 18, 2023

******
የካቲት ፲፩ቀን፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******

ጥር ፰ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በተገኙበት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሦስት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በተገኙበት በተደረገው ውይይት ፲ የስምምነት ነጥቦች ተቀምጠው በነጥቦቹ ላይ የጋራ መግባባት ከተደረሰ በኋላ የጋራ መግለጫ በመስጠት ስምምነቱ መጽደቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ስምምነቱን ሙሉ ለማድረግና ዕርቁን ተቋማዊ ለማድረግ በማሰብ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነ አቡነ ሳዊሮስን በመያዝ ወደ መንበረ ፓትርያርክ በማምጣት ከቅዱስነታቸው ጋር እንዲገናኙ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ዛሬ የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በመወከል በስምምነቱ ላይ የተሳተፉት ብፁዓን አባቶችና እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገናኝተው ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት በምንም መልኩ መጣስ እንደሌለበት በመተማመን በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት ፰ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማማንባቸውን (፲) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል። በማለት ይፋዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ከመግለጫው በኋላም ወደ ማረፊያ ቤታቸው ገብተዋል።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም የአባቶችን መመለስ ተከትሎ የጸጥታ ሥራው አስተማማኝ መሆን ይችል ዘንድ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሕጋዊ መልኩ ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ በማመንና ጸጥታውን አስተማማኝ ለማድረግ እንዲሁም የጥበቃ ሥራውን ተቋማዊ በሆነ መልኩ የሚያከናውኑ የፌደራል ፓሊስ አባላት እንዲመደቡለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ስላገኘ ከፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን የፓሊስ አባላት ተመድበው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የጥበቃ ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በትላንትናው ዕለት የነበረው ሁኔታ ከፍ ሲል በተጠቀሰው አግባብ የተስተካከለ መሆኑን እየገለጽን የተጀመረው የሰላም ሂደት ግቡን ይመታ ዘንድ ምዕመናንና ምዕመናት በወርሃ ጾሙ ወደ ልዑል እግዚአብሔር አጥብቀው በመጸለይ እንዲተጉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-02-18 17:35:262023-02-18 17:35:26አሥሩን ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመተግበር እነ አቡነ ሳዊሮስ ተስማሙ።ወቅታዊ መግለጫ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በቀድሞ ስማቸው እነ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል። Link to: በቀድሞ ስማቸው እነ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል። በቀድሞ ስማቸው እነ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ... Link to: ማኅበረ ቅዱሳንና ሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያዘጋጁት የ2015 ዓ.ም የከፍተኛ ት/ተቋማት ገቢ ተማሪዎች ሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ። Link to: ማኅበረ ቅዱሳንና ሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያዘጋጁት የ2015 ዓ.ም የከፍተኛ ት/ተቋማት ገቢ ተማሪዎች ሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ። ማኅበረ ቅዱሳንና ሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top