መጋቢት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና አካባቢው አገልግሎት የሚሰጡ ልዩልዩ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ደህንነቱ የተጠበቀና ለከተማው የገቢ ማስገኛ የሚሆን መኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ግንባታ፣ለአካባቢ የጽዳት ብክለት መከላከያ የሚህን የለማት ሥራና በጸሐይ ሀይል የሚሠራ የመንገድ ዳር ሶላር መብራት ሥራ በገዳሙና አካባቢው መከናወን ይችል ዘንድ 34.531.000.00 ሰላሳ አራት ሚሊየን አምስት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ብር በጀት ተይዞ ወደ ሥራ እንዲገባ አመራር ተሰጥቷል።

ከገዳሙ የሚገኘው ገቢ በቤተክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ለመንፈሳዊ ኮሌጆች፣ለተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ማስከፈቻ ገዳማትና አድባራት ድጎማና ለልማት ሥራዎች እንደሚውል የሚታወቅ ሲሆን ገዳሙንና አካባቢውን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻርም ለቁልቢ አካባቢ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከነ ሙሉ ግብዓቱ ለወረዳው ነዋሪ ሕዝብ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ለምዕመናን መጠቀሚያ የሚሆን መጸዳጃ ቤቶችና ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ጊዜ በገዳሙና አካባቢው የሚከናወነው የልማት ሥራም በዓሉን በሰላም በማክበርና ከበዓሉ አከባበር ሥነሥርዓት በኋላ የሚስተዋለውን የንጽሕና ችግሮች በመቅረፍ ረገድ ጉልህ ድርሻ ንደሚኖረው የቁልቢ ንዋያተ ቅድሳት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ በኩረ ትጉሃን ወንድማገኝ ተፈራ ገልጸዋል።