የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ስራ አስጀምረዋል፡፡

በሕንጻው የመልሶ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሕንጻ ግንባታ ጽርሐ ሚኒሊክ ወይም በተለምዶ መሐሙድ ሕንጻ በመባል የሚታወቀው ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ሕንጻው በፈረሰበት ቦታ ላይ ለመንገድ ስራ ከሚውለው ቦታ ውጪ ባለው ቦታ ላይ የአካባቢን የመኪና ማቆሚያ ችግር ሊፈታ በሚችል አግባብ በራሱ ወጪ በአንድ ዓመት ውስጥ ገንብቶ ለቤተክርስቲያኗ ለማስረከብ በተስማማው መሰረት በዛሬው ዕለት የግንባታው ማስጀመሪያ የመረት ድንይ ተቀምጧል።

በዚሁ ጊዜም ክብርት ከንቲባዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ሥራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ እናመሰግናለን ብለዋል ።