በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮችን ዝርዝር በአፋጣኝ እንዲልኩ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ሰጡ።
በመላው ዓለም ለምትገኙ አህጉረ ስብከት በሙሉ፤
********
መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የቤተክርስቲያናችንን የመረጃ ሥርዓት ለማዘመን የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ፣መተንተኛና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ሥርዓትን በመፍጠር ወጥነት ያለው የመረጃ ፍሰት ለመዘረጋት በጥናት ላይ የተመሰረተ የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።
መምሪያው የአሰራር ሥርዓቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማደራጀት የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካትም በውጭ አህጉረ ስብከት የሚገኙ አድባራት፣ገዳማት፣የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣የአገልጋይ ካህናት፣ሰባኪያነ ወንጌልና የአስተዳደር ሰራተኞችን ብዛት ለማወቅ ይቻል ዘንድ በድረ ገጻችን ላይ የተቀመጠውን የመረጃ ማሰባሰቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት መረጃዎችን ለማደራጀት የምናደርገውን ተቋማዊ ጥረት ለማሳካት የድርሻችሁን እንድትወጡ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ስም መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ