የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠውን መግለጫ በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

March 24, 2023

ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠውን መግለጫ
በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
*********
መጋቢት 15ቀን 2015ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
***

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመናት በአገራችን ኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጸንቶና ልዩነቶች ተወግደው እንዲኖሩ አርአያና ምሳሌ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀት ፈጥራና በአንድ መዋቅራዊ አስተዳደር ጸንታ መኖሯ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተከሰቱ ባሉ አለመግባባቶች መነሻነት ከአገራችንም አልፎ ጸንቶ በቆየው የቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ መዋቅር ላይ እየተከሰቱ ካሉ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ነው፡፡
በዚሁ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎና በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው በየጊዜው እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ለትግራይ አህጉረ ስብከት ይላክ የነበረው በጀት መላክ አልተቻለም፡፡ ይህም በጦርነቱ ከደረሰው ጉዳት በላይ በመዋቅሮቻችን ሥር ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና አገልጋይ ሠራተኞች ላይ የበጀት እጥረት አጋጥሞ ቆይቷል፡፡
ምንም እንኳን በባንክ መዘጋት ለአገልጋይ ሠራተኞች በጀት መላክ ባይቻልም የደመወዝ መክፈያ የባንክ ሂሣባቸው በአዲስ አበባ ከፍተው ሲገለገሉ የቆዩት አባቶች ማለትም፡
– ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
– ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና
– ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በጦርነቱ ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለምንም መቆራረጥ ወርኃዊ ደመወዛቸው ወደ ባንክ ሂሣባቸው ሲገባ የቆየና እየገባ ይገኛል፡፡
– የብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የባንክ ሂሣብ ግን በዚያው በሚኖሩበት አካባቢ የተከፈተ በመሆኑና በአካባቢው የባንክ አገልግሎት በመቆሙ በጀቱን ማድረስ ያልተቻለ ነው፡፡ በዚህም የዋናው መ/ቤት በእጅጉ ያዘነና በአገሪቱ የተከሰተው ጦርነት ሰላማዊ እልባት አግኝቶ መንግስታዊ መዋቅራዊ ግንኙነቱ እንደተጀመረ የተከሰቱ ችግሮችንና የደረሰውን የጉዳት መጠንና ማዕከል ያደረገ ውይይት በማድረግ ተገቢና ችግር ፈቺ በጀት ለመመደብ ይቻል ዘንድ ለሁሉም የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነጳጳሳት በቁጥር 197/897/2015 በ1/6/2015 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪ አስተላልፋለች፡፡
ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር ፈቺ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ሲገባ በክልሉ የተከሰተውን ችግር ቤተ ክርስቲያናችን እንዳላዘነችና የጉዳቱ ቀጥተኛ ተጠቂ መሆኗን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ምላሽ አዘል መግለጫ እንደደረሰን ጉዳዩን በጽሞናና በትዕግስት በማየት በጥናት ላይ የተመሰረተ ችግሩን ሊፈታ የሚችል የአቀራራቢ ሽማግሌ ልዑካንን ለመመደብ በዝግጅት ላይ እያለን መጋቢት 13 ቀን 2015ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያናችንን ጸንቶ የቆየ ተቋማዊ አንድነትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሚንድ መልኩ “መንበረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጽ/ቤት የሚል አዲስ ሕገወጥ ክልላዊ መዋቅር በመፍጠርና ያለምንም በቂ ማስረጃ ዋናው መ/ቤት በጀት እንደከለከለ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ እንዳገደ በአጠቃላይ በክልሉ በሚገኙ አህጉረ ስብከት ላይ አቅዶ ችግር እንደፈጠረ የሚያስመስልና ሕገ-ቤተ ክርስቲያኑን የጣሰ መግለጫ ከመሰጠቱም በላይ በሕገ-ቤተ ክርስቲያኑ ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በሁሉም አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሊመደቡ የሚችሉት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ መሆኑ እየታወቀ ሆን ተብሎ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሥራ ላይ እያሉና ሲኖዶሳዊ አንድነቱ ጸንቶ ባለበት ሀኔታ ላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጭና ያለቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ አሠራርን በጣሰ ሁኔታ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው በሚሠሩባቸው የውጭ ዓለማት አህጉረ ስብከት ላይ ሊቃነ ጳጳሳት ከቀኖና ውጭ ራሳቸውን በራሳቸው በመመደብ መግለጫ መስጠታቸውን በመገናኛ ብዙኃን በመስማታችን በእጅጉ አዝነናል፡፡
በመሆኑም የእምነትና የታሪክ መሠረት በሆነው በታላቁ የትግራይ አህጉረ ስብከት እንዲህ ዓይነት መዋቅርን የሚንድና ቤተ ክርስቲያናችንን ለአደጋ የሚያጋልጥ በዓለም መላውን የእምነቱን ተከታዮች የሚያሳዝን አድራጐት ለታሪካዊ ለትግራይ ሕዝብና ሊቃውንት የማይመጥን አድራጎት ከመሆኑም በላይ ለቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አንድነትና መስፋፋት ተጋድሎ የፈጸሙ የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችንን ያሳዘነ መሆኑን ለተከበረው የትግራይ ሊቃውንትና ሕዝብ የተሰወረ እንዳልሆነ በጽኑ እናምናለን፡፡
በመሆኑም ከላይ በዝርዝር ለመግለጽ እንደሞከርነው ፡-
1. በትግራይ ክልል የሚገኙ አህጉረ ስብከት በጀት እንዳይላክ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ አንድም ውሳኔ የሌለና በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የባንክ አገልግሎት በመቆሙ የተከሰተ የግንኙነት መቋረጥ መሆኑ ታውቆ በጀቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ ከአህጉረ ስብከት ጋር በመነጋገር ለመላክ ዝግጁ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

2. በክልሉ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን ጉዳትና ችግር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ሐዘንና በችግሩም ወቅት ለአህጉረ ስብከቱ በበጀት ተደራሽ ባለመሆናችን ያስከተለው ችግር ያሳዘነን መሆኑን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ገልጸን እያለንና የተከሰተው ጦርነት እንዲቆም በጸሎትና በምሕላ ስንማጸን መቆየታችን ወደጐን ተትቶና ተዘንግቶ ቤተ ክርስቲያናችን የጦርነቱ ደጋፊ በሚያስመስል መልኩ የተሰጠው መግለጫ ተቀባይነት የሌለውና ቤተ ክርስቲያናችንንም የማይገልጽ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3. እናት ቤተ ክርስቲያን በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዳጩ ሆሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገወጥ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ፈተና ለመፍታትና የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለማጽናት በከፍተኛ ኃላፊነት እየሠራች ባለበት ሁኔታ ለዚህ የቤተ ክርስቲያናችን ተልዕኮና ተቅማዊ አንድነት መጽናት በጸሎትም በሐሳብም ልንታገዝ ሲገባ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አበው የእምነትና የታሪክ መሠረት በሆነው የትግራይ ሊቃውንት እንዲህ ዓይነት ድርጊት መከሰቱ ለአገሩም ሆነ ለሕዝቡ የሚመጥን አድራጐት ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን፡፡
4. በክልሉ ያለው አጠቃላይ መዋቅራዊ ችግሮችን በሚመለከትና አጠቃላይ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰቱትን ችግሮች ተወያይቶ ለመወሰን መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም.

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የተጠራ ስለሆነ በክልሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድባችሁ በመሥራት ላይ የምትገኙ ሊቃነጳጳሳት በጥሪው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ላይ እንድትገኙና ክልላዊ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ውይይት ላይ በመሳተፍ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአደራ ጭምር ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

5. የተከበራችሁ በትግራይ ክልል የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችሁ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ጸንታ እስከአሁን መቆየቷን ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ በመሆኑም በአገራችን በተከሰተው ፖለቲካዊ ችግር ዘመናትን በጽናት የተሻገረችውን እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነቷ መፍረስ ሲኖዶሳዊ ልዕልናዋ መጣስ የሌለበት መሆኑን በጽናት እንደምታምኑ እምነታችን የጸና ነው፡፡
ስለሆነም በሚያልፍ ችግር የማያልፍ ታሪክ ጥለን ማለፍ ስለሌለብን እንደቀደሙ አባቶቻችሁ አበው ሊቃውንት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል በጽናት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቀደሙ አባቶቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
6. የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስቱም በክልሉ ተፈጥሮ የቆየው ችግር በሰላማዊ መንገድ በውይይት በመፈታቱ እናት ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ደስታ እየገለጸች አስቀድሞ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን የተመራው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለቀረበው የሰላም ጥሪ እናት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወተች እናስታውሳለን፡፡
በመሆኑም በተከሰተው ችግር የተፈጠሩ ጉድለቶች ካለ ጉድለቶችን ለማረምና ችግሮቹን ለመፍታት ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን የጸና አቋም እየገለጽን በክልሉ የተከሰተውን ተቋማዊ አንድነትን የሚጥስና ቀኖና የጣሰ አደረጃጀት እንዲቆም የበኩሉን ሚና በመጫወት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም መላው በትግራይ ክልል የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲወገድና አንድነቷ ጸንቶ እንዲኖር በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ ስታግዙ እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም በክልሉ የተከሰተውን ቀኖናዊ ጥሰትና ሕገወጥ አደረጃጀት ቆሞ እናት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር እንደአሁን ቀደሙ በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን የኢፌዴሪ መንግስትም እንደአሁን ቀደሙ በሲኖዶሳዊ አንድነት ላይና በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ የተጋረጠው ችግር ልዩ ትኩረት በመስተጠና የበኩሉን ሚና በመጫወት የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድንትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀት ጸንቶ እንዲኖር አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮችን ዝርዝር በአፋጣኝ እንዲልኩ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ሰጡ። Link to: በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያናትና የአገልጋዮችን ዝርዝር በአፋጣኝ እንዲልኩ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ ሰጡ። በውጭ ሀገራት የሚገኙ አህጉረ ስብከት የአብያተ... Link to: “የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን” ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው ጥያቄ ነው”። Link to: “የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን” ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው ጥያቄ ነው”። “የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን”...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top