ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስ ዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምስራቅ ጉራጌ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራአስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣ የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል መሪጌታ ሀብቴ ፣የየአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ሊቀውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ቁጥሩ
እጅግ ብዙ የሆነ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተገኙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከብሯል ።
#በዕለቱም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለድቁና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ28 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ድቁና የሰጡ ሲሆን ለቅስና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ7ት ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጥተዋል።
#ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገ በኋላ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።
#በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት የመልካም ምኞትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጎፋ ዞን በመሬት መሸራተት ለተጎዱ ወገኖቻችን ሕዝቡ በጸሎት ከመሳብ ጀምሮ የአይነት ድጋፍ በማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።በክብር እንግድነት የተገኙትን የዲላ ከተማ ከንቲባን አመስግነዋል።
የዕለቱን ትምህርት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዓሉን የተመለከተ ስለ ቅዱሳን መላእክት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል በመላእክትና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት መነሻ በማድረግ የመላእክት እርዳታ አስፈላጊነት ገልጸዋል።
ትምህርት ሰጥተዋል።በብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ጸሎት በመድረግ የበዓሉ ፍጻሜ ሲሆን ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዓን አባቶች ተመርቷል።
የሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል