የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

July 30, 2024

ሐምሌ 19/2016 ዓ/ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የምዕራብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡቡር አቶ መኩሪያ መርሻዬና ሌሎችም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎ፣ የሀዋሳ ከተማና ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን በዐውደ ምሕረትም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰ/ት/ት ቤት መዘምራን ያሬዳዊ ወረብ ከቀረበ በኋላ የሀዋሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ላዕከ ወንጌል ደግፌ ባንቡራ መልእክት አስተላልፈው ክቡር ከንቲባውን ጋብዘዋል።
ክቡር ከንቲባውም የቅዱስ ገብርኤል አምላክ ረድቶን ከታኅሣሥ ዛሬ ደረሰን እንድናከብር የረዳን እግዚአብሔር ስለሆነ እናመሰግናለን።

የዛሬውም በዓል እናትና ልጅ ከሃይማኖታቸው ውጭ የመጣባቸውን እንቢ በማለታቸው ወደ እሳት ቢጣሉም ታላቁ መልአክ እንደ ታደጋቸው የሚነገርበት ዕለት እንደ ሆነ አባቶቻችን ያስተምሩናል።
ስለዚህ ይህ በዓል የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆን የከተማችን በዓል ነው በአጠቃላይ ይህን በዓል ስናከብር ከሚያመልኩት ውጭ እንዲያመልኩ ሲጠየቁ እንቢ እንዳሉት እኛንም ከአብሮነታችን ከሰላማችን ውጭ መለያየትን ጥላቻን የሚያመጡትን እናትና ልጅ እንዳረጉት እንድታደርጉ አደራ ማለት እፈልጋለሁ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

በመቀጠል የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ኪደነ ማርያም አንዱዓለም ለበዓሉ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ የመንግሥት አካላትንና ምእመናን ካመሰገኑ በኋላ በግቢ ውስጥ እየተሠራ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ገለጸው የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ጋብዘዋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍም ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ በእምነታቸው በመጽናታቸው እናከብራቸዋለን ስለዚህ እኛም መጽናት አለብን።ሌላው ቤተ ክርስቲያን ኀዘን ላይ ናት ጎፋ አካባቢ በተፈጠረው ውስጣችን ተሠብሯል።

በጸሎት እናስባቸዋለን ኮሚቴ አዋቅረን ገንዘብ አሰባስበን በአካል ሄደን እናጽናናለን ኅዘናችን ግን ጥልቅ ነው በማለት አባታዊ መልእክት አስተላላፊው የዕለቱን ትምህርት እንዲያስተምሩ መድረኩን ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስም “ወኩን መሀይመ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት” እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጥሀለሁ ራዕ 2፥10 በሚል ርእስ ተነስተው የቅድስት ኢየሉጣንና የቅዱስ ቂርቆስን የእምነት ጽናት አንስተው ሰፊ ትምህርት አስተምረዋል።

በመጨረሻም በጎፋ አካባቢ በአዳጋ የሞቱትን እረፍተ ነፍስ እንዲሰጣቸው የተጎጂ ቤተሰቦችን እግዚአብሔር እንዲያጽናናቸው
አባታዊ መልእክትና ቡራኬ ሰጥተው በብፁዕነታቸው ጸሎት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።©የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ የታማኑላትን በእሳት ውስጥ ያለፉባትን ቅድስት እምነታችንን በመጠበቅ መንገዳቸውን ልንከተል ይገባል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ Link to: “ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ የታማኑላትን በእሳት ውስጥ ያለፉባትን ቅድስት እምነታችንን በመጠበቅ መንገዳቸውን ልንከተል ይገባል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ “ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ የታማኑላትን በእሳት... Link to: በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ! Link to: በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ! በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top