የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

“ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ የታማኑላትን በእሳት ውስጥ ያለፉባትን ቅድስት እምነታችንን በመጠበቅ መንገዳቸውን ልንከተል ይገባል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

July 30, 2024

ሐምሌ ፲፱/፳፻፲፮ ዓ/ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በነገረ ድኅነት መሠረትነትና የዘለዓለማዊ ሕይወት ዋጋ ማግኛ እንዲሆኑ በዓላትን ታከብራለች።

በየዓመቱ ሐምሌ ፲፱ ቅዱስ ገብርኤል ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ በፈላው ውኃ ጋን ውስጥ እንዲጣሉ የተፈረደባቸውን ቅድስት ኢየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ያዳነበት ዐቢይ በዓል በመሆኑ መታሰቢያቸው ባሉበት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በድምቀት ይከበረል።

በዓሉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሲከበር ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ ትጉኃን ወንድወሰን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ሊቃውንት አባ ኪዳነ ማርያም የካቴድራሉ አስተዳዳሪ፣ ሊቀ ኅሩያን ዮሐንስ ቀኖ የብፁዕነታቸው ልዩ ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት የሥራ ሓፊዎች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተውበታል።

በዓሉን አስመልክቶ በካቴድራሉ ሊቃውንት “ዘረዳዕኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት
እግዚኦ አድኅነነ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እምዕለት እኪት” የሚለው ወረብ ቀርቧል።

በካቴድራሉ ሐመረ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንም “ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን የሚለውን አቡኑ ቃኝተውና ጸፍተው “ወዓዲ ከመ ኢይማስን ሥጋከ
ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ” የሚለውን አመላለስ ወረብ አቅርበዋል።

ትምህርተ ወንጌል በአማርኛ፣በኦሮምኛና በወላይትኛ ቋንቋዎች የተሰጠ ሲሆን በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የሰጡት ሊቀ ትጉኃን ወንድወሰን የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ “ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤” ፊልጵስዩስ ፩፥፳፱ በሚል ርእስ መነሻነት ስለቅድስት ኢየሉጣና ስለ ቅዱስ ቂርቆስ በመከራ ስለመጽናት እንዲሁም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እንዴት እንዳዳናቸው አስተምረዋል።

ሊቀ ትጉኃን በትምህርታቸው አክለውም እንደቅዱስ ቂርቆስ ለቤተሰቡ ለጎረቤቱ ለሀገር ለጓደኛው የመዳንና በእምነት የመጽናት ምክንያት የሚሆኑ ልጆች ለትውልዳችን እንደሚያስፈልጉ በምሳሌነት ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው የሰማዕታቱን የተጋድሎ ብዛትና የእምነት ጽና ከአሁኑ ዘመን ክርስትና ጋር በማነጻጸር አሳይተዋል።

እንደደመና የከበቡን ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ የታመኑላትን በእሳት ውስጥ ያለፉበትን ቅድስት እምነታችንን በመጠበቅ መንገዳቸውን ልንከተል ይገባል ብለዋል።

ዘመናችን ብዙ የሚያሳዝኑ ነገሮች የምንሰማበት ጊዜ ሆናል ያሉ ሲሆን በዚሁ ሳምንት በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ ምክንያት በሞቱ ወገኖቻችን እጅግ አዝነናል ብለዋል።

ስለሆነም ወደ እጥዚአብሔር በመጮህ ከመጡብን መከራዎችና ተግዳሮቶች በላይ ሆነን በመጽናት ሰማዕታት መሆን ይገባናል ብለዋል።

በመጨረሻም ታቦታቱ ወደ መንበረ ክብራቸው የገቡ ሲሆን ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዕነታቸው መሪነት ተከናውኖ ከቀኑ 9:00 ሰዓት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።©ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል እና የህጻኑ የቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ አመታዊ በዓል የከሚሴ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነው በከሚሴ ከተማ ተከበረ። Link to: የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል እና የህጻኑ የቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ አመታዊ በዓል የከሚሴ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነው በከሚሴ ከተማ ተከበረ። የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል እና የህጻኑ የቅዱስ... Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። Link to: በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ በደብረ ምሕረት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top