የካቲት ፲፪ ቀን ፲ወ፮ ዓ.ም
================
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
++++++++++++++

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ከአባታቸው ከመምህሬ ገብሬ ማርያም አፍለና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሕደግ ወልዱ 1935 ዓ/ም በቀድሞ አጠራርበትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አውራጃ ልዩ ስሙ ቤተ ጰንጠሌዎን በሚባል ቀበሌ ተወለዱ ።

በተለያዩ ጥንታውያን አድባራትና ገዳማት ከስመጥር ሊቃውንት ተምረዋል፡፡ መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ከመዝሙረ ዳዋት እስከ ጸወትወ ዜማ በአክሱም ከተማ ከተለያዩ መምህራን ተምረዋል። ከዚያም በኋላ ትመህርታቸውን ለመጨመር ከአከሱም ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር በመሄድ ዳባት ገብርኤል ደብር ከነበሩበት ብዙ ሊቃውንትን በመስተማር ስመ ጥር ከነበሩት የድጓ ሊቅ ከየኔታ ገብረ ማርያም ድጓ ተምረዋል፡፡ ከዚያም የቅኔን ትምህርት ለመማር በነበራቸው ክፍተኛ ፍላጎት ከተለያዩ የቅኔ መምህራን ቅኔን ተምረዋል፡፡በኋላም የቅኔ ፈጣሪ ከነበሩት ከክቡር 25 የኔታ ዕፀብ/ዕፀብ ጎበዙ/ ለዐሥር ዓመታት በተማሪነትና የክቡር ጌታ የኔታ ዕፁብ ምክትል መምህር በመሆን ቅኔን አስተምረዋል፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም በሀገር ውስጥ ከተለያዩ አድባራትና ገዳማት በመምህርነት ወንበር ዘርግተው አስተምረዋል :: በነበራቸውን የትምህርት ጽኑ ፍቅርና ፍላጎት በመመልከት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ዕድል መሠረት ከሌሎች የቤተ ክርስቲያን ምሁራን ጋር በ1973 ዓ/ም ወደ ሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ዩኒቨርሲቲ ተልከው ለአምስት ዓመታት ከፍተኛውን ትምህርት ከተማሩ በኋላ እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር በ1973 ዓ/ም በማስተርስ ዲግሪ በማዕርግ ተመርቀዋል፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም 5 መጻሕፍት የደረሱ ሲሆን እነሱም

1. ክርስትና በኢትዮጵያ ከክፍል 1 አስከ ክፍል 5

2. ተቀዊመ ማኃቶት

3. የግእዝ ቋንቋ ማስተማሪያ መጻፍ

4. ቅዱስ ያሬድና የአክሱም ትውፊታዊ ታሪክ

5.ትምህርተ ቱዎፍሎስ

ትርጉም (teranslation)

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም የተለያዩ ጥንታውያን መጻሕፍትን ከግእዝ ቋንቋ ወደአማርኛ ትርጉመዋል።ከነዚንም መካክል-

• ጊዮርጊስ ወልደአሚድ፣

• ዮሴፍ ወልደኦርዮን፣

. ገድለ ሐዋርያት፣

• ገደለ ሰማዕታት፣

• መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በወቅቱ ሊቀ ጳጳስ ዘእክሱም ወዘኵሎን አድያማተ ትግራይ፣ ቅስናን ከብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሊቀ ጳጳስ ተቀብለዋል።

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም የካቲት 12 ቀን 2916 ዓ/ም በደረሠባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ጻዕርና ድካም ዐርፈዋል ሥርዓተ ቀብራቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዋና ክፍልና የገዳማት ኃላፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።©EOTC TV