የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በታላቁ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተመራ ውይይት ተካሄደ፡፡

February 23, 2024

የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

በጥንታዊውና ታሪካዊ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በተፈፀመው ጥቃትና የመነኮሳት ግድያን አስመልክቶ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አባቡ ዋቆ የተመራ ውይይት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፡ የምሥራቅ ሸዋ ዞን የጸጥታ ክፍል ከፍተኛ ኃላፊዎች ፡ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮነን የተመራ ልዑክ ፡ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤና የሀገረ ስብከቱ ልዑካን ፡ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አበምኔትና የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በግፍ የሰማዕትነትን ጽዋ የተቀበሉ አባቶች መርዶ በትናንትናው ዕለት የተሰማ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሀዘናቸውን በመሪር እንባ እየገለጹ ይገኛሉ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትም ከገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በትኩረት ጉዳዩን ሲከታተል የቆየ ሲሆን በዛሬ ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ የኢ/ፌ/ዴ/ሪ አየር ኃይል ግቢ አራት ሰዓታትን የፈጀ ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በውይይቱ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች፡-

1ኛ፡- በመንግሥት የፀጥታ አካላት አማካኝነት የሰማዕታቱን አስክሬን ከወደቁበት አንስቶ በክብር ወደ ገዳሙ በማምጣት ሥርዓተ ቀብር እንዲፈፀምላቸው

2ኛ- በቋሚነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊትና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጸጥታ መዋቅር ገዳሙንና ገዳማውያንን በዘላቂነት መጠበቅ እንዲቻል

3ኛ፡- በመንግሥትና በሀገረ ስብከቱ እንዲሁም በቤተክርስቲያን አባቶች ልባቸው የተሠበረና የተጎዱ የገዳሙ አባቶችና እናቶችን በጋራ ማጽናናት እንዲችል፡፡ የውይይቱ የውሳኔ ሃሳቦች ሲሆን ይኼው ግብረ ኃይል ከሀዘኑ በኋላ ዳግም ተገናኝቶ በተሠሩ ሥራዎችና ወደ ፊት አስተማማኝ ሰላም በሚሠፍንበት ጉዳይ ላይ ለመመካከር ቀጠሮ ተይዞ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዕለቱ ውይይት በጸሎት ተዘግቷል፡፡

© የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: በ81 ዓመታቸው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ያረፉት የሊቁ የመምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ። Link to: በ81 ዓመታቸው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ያረፉት የሊቁ የመምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው የበዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ። በ81 ዓመታቸው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ያረፉት... Link to: በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። Link to: በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች አስክሬን ተረሽነው ከተቀበሩበት ከጊዳ ተክለሃይማኖት አካባቢ ተነስቶ በገዳሙ በክብር ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። በግፍ የተገደሉት የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top