ጥር 6 ቀን 2016ዓ/ም
“””””””””””””””””””””
ጋምቤላ -ኢትዮጵያ
****
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጋምቤላ ፣ የቄለም ወለጋ፣ የአሶሳ እና የደቡብ ሱዳን አሁጉረ ስቅከት ሊቀ ጳጳስ የጋምቤላ ክልልና የቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት የኃማኖት ተቋማት ሰብሳቢና የልማትና የሰላም አምባሳደር ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተነስተው በመኪና ጉዞ በማድረግ ከ10,000,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ልዩ ልዩ ንዋተ ቅድሳትን በመያዝ ወለጋ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን እየባረኩና የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን በማስከፈትና የንዋተ ቅድሳት ድጋፍ በመድረግ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጋምቤላ ገብተዋል ።
ብፁዕነታቸው በጋምቤላ የሚከበረውን የ2016ዓ.ም የጥምቀት በዓል ካከበሩ በኋላ በሸቤልና በሙጊ አድርገው ወደ ቄለም ወለጋ በመጓዝ ልዩ ልዩ የንዋያተ ቅድሳት ድጋፍ ካደረጉና በዚያ የሚገኙ ምዕመናንን ባርከው ትምህርተ ወንጌል ከሰጡ በኋላ ጉዟቸውን በመቀጠል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ ጉዞ እንደሚያደርጉ የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ገልጿል።