የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሀገረ ስብከታቸው የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናክረው ቀጥለዋል።

January 15, 2024

ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም
***
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሀገረ ስብከቱና ፣የቤተመጻሕፍት ወመዘክር፣የማኅበራት ማደራጃ  መምሪያ ሊቀ ጳጳስ በአላማጣና አካባቢው የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናክረው በመቀጠል ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም  በዋጃ አካባቢ በሚገኘው ደብረ ሣሌም ቦታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲደርስሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዚሁ ጊዜም በአካባቢው በነበረው በጦርነት ምክንያት በሞተ ሥጋ  ለተለዩ አሥራ አምስት ሰዎት ጸሎት አድርሰዋል።በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በሕዝበ ክርስቲያኑ አማካኝነት እየተሰራ የሚገኘውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተዛውረው የተመለከቱት ብፁዕነታቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ  በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ  ችግቹን ችሎና ታግሶ ይህን የመሰለ ሕንጻ ቤተክርስቲያን መስራቱ ከሰማዕትነት የሚያስቆጥረው መሆኑን ገልጸው ለሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ማሰሪያ አንድ መቶ ሺህ ብር በመለገስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።በዚሁ ጊዜም ሕዝበ ክርስቲያኑ አንድነቱን አጽንቶ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ ጠብቆና አክብሮ በመገኘቱ አመስግነዋል።

በመቀጠልም አዲስ ወደ ተሰራው አየር ማረፊያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጓዙት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የዋዜማ ሥርዓተ ቡራኬ በማድረግ የማጽናኛ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በማግስቱ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱን በማክበር ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።በዚሁ ጊዜ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክትም ሕዝበ ክርስቲያኑ በጦርነት ውስጥ ሆኖ ይህንን የመሰለ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሰርቶ ማስመረቁ ከሰማዕትነት በላይ መሆኑን አይተናል አድንቀናልም ብለዋል።

በዚሁ ጊዜም የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴውና ምዕመናኑ የብር መስቀል ለብፁዕነታቸው አበርክተውላቸዋል።
ብፁዕነታቸውም የሃያ ሺህ ብር የበረከት ስጦታ አበርክተዋል።በመጨረሻም በብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በዚህ መልኩ የቀጠሉት ብፁዕነታቸው ዛሬ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ኮረም ከተማ የተጓዙ ሲሆን ግራት ካህሱን አለፍ እንዳሉ ከአምስት መቶ በላይ በሚሆኑ መኪናዎችና ባጃጆች እንዲሁም በእግር ጭምር በመሆን ሕዝበ ክርስቲያኑ በተለይም ደግሞ ወጣቶች በነቂስ ወጥተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕነታቸውም የኮረም ከተማን ተዛውረው ከባረኩ በኋላ በኮረም  ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን ኪዳን አድርሰዋል።በአውደ ምህረቱም ሦስት ሊቃውንት ቅኔ አበርክተውላቸዋል፤ካህናቱና ምዕመናንም በወረብ፣ በዝማሬና በእልልታ በአክብሮት ተቀብለዋቸዋል።
ብፁዕነታቸውም ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን በማቅረብ ችግሮቹ ተወግደው ተወልደው ባደጉበት አገር ከሚወዳቸውና ከሚያከብራቸው ሕዝባቸው ጋር ለመገናኘት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ እግዚአብሔርን አመስግነዋል ።

በዚሁ ጊዜም ብፁዕነታቸው “ምንም እንኳን በሞት ጥላ ብሆንም አንተ ከእኔ ጋር ነህና አልፈራም”በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻነት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።በጦርነቱ ለሞቱ ወገኖችም ጸሎት ያደረጉት ብፁዕነታቸው  አዲስ ለሚታነጸው የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንም የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል።ለሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ የሚውል የአንድ መቶ ሺህ ብር ስጦታ ያበረከቱት በብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ቤተክርስቲያን አንዲት ስለሆነች የቤተክርስቲያናሁን አንድነት እንደጠበቃችሁና የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ በአንድነት እንደቆማችሁ ሁሉ አሁንም ይህንኑ ተግባራችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ ብለዋል።

በመጨረሻም ሁተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ቃለ በረከትና ቃለ ምዕዳን በመስጠት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ህኖ ብፁዕነታቸው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው አቅንተዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/photo_2024-01-15_14-24-29-cover.jpg 444 400 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-01-15 15:16:172024-01-15 15:16:17ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሀገረ ስብከታቸው የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናክረው ቀጥለዋል።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጋምቤላ ገቡ፤ከአሥር ሚሊየን ብር በላይ ንዋያተ ቅዱሳን ይዘው ተጉዘዋል። Link to: ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጋምቤላ ገቡ፤ከአሥር ሚሊየን ብር በላይ ንዋያተ ቅዱሳን ይዘው ተጉዘዋል። ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የጥምቀት በዓልን ለማክበር... Link to: የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። Link to: የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top