መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
******
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ከሚገኙ ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ ብዛታቸው 800 የሚደርሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በ2016 ዓ.ም የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል በተለየ ድምቀት ለማክበር ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ግቢ በዓሉን የተመለከተ የወረብ ጥናት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገው የወረብ ጥናት መርሐ ግብር ወቅት ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ለሠልጣኞቹ የማበረታቻ ሐሳብና ቡራኬ ሰጥተዋል።