የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የመስቀል ደመራ በዓል የአከባበር ሥነ ሥርዓት ዝግጅት ተጠናቀቀ።

September 27, 2023

መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””'”””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
***
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ከምታከብራቸው የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱና በዓለም አቀፉ የትምህርት ሳይንስና ባህል ጅርጅት በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል ።

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም በዓልን በደመቀ መልኩ ለማክበር ይቻል ዘንድ ከአሥራ ሦስት በላይ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማደራጀት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን ስታደርግ ሰንብታ እነሆ ለዛሬው ዕለት ደርሳለች።የበዓል አከባበሩን የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ከቀትር ቀኋላ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ተዛውረው የጎበኙ ሲሆን አጠቃላይ የዝግጅት ሥራው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይም የክብር እንግዶች የሚቀመጡበትን የመቀመጫ መድረክ ከነ ሙሉ የድምፅ ግብዓቱ በማቅረብ ለበዓላችን ድምቀት ትብብር ያደረገልንን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርንና ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤን አመስግነዋል።

የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ በተዘጋጀው መርሐ ግብር መሠረትም በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡ ምዕመናንም ከጠዋቱ አምስት ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን፣ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በዓሉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር ሲባል ለሚያደርጉት ፍተሻ ፍጹም ክርስቲያናዊ የሆነ ትብብር እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
በአንዳንድ የመገናኛ አውታሮች የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት የሆኑ ከበሮ፣ጸናጽልና መቋሚያ እንዳይገባ ተከልክሏል በማለት የሚናፈሰው ወሬም ፍጹም ሐሰት መሆኑን እየገለጽን በዓሉን በትርኢት ለማክበር የተፈቀደላቸው ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ኤነዚሁኑ ንዋያተ ቅድሳት ይዘው የሚገኙ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

በላላ በኩል ወደ በዓሉ ማክበሪያ በሚደረግ ጉዞ ላይ በአደባባዩ የሚገኙ የበዓሉ ታዳሚ ምዕመናን ያለምንም መግቢያ ባጅ ተፈትሸው ብቻ ወደ አደባባዩ መግባት የሚችሉ ሲሆን የመግቢያ ባጅ የሚጠየቁት የክብር እንግዶች፣ጋዜጠኞችና ልዩልዩ የሚዲያ ተቋማት ብቻ መሆኑን እንገልጻለን።

በመጨረሻም በዓላችን በአማረና ቀደመቀ መልኩ መከበር ይችል ዘንድ በማንኛውም መሌኩ ትብብር ላደረጉ አካላት በሙሉ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ምስጋናዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
መሰከረም ፲፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ ዶክተር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አስመልክቶ የሊቃውንት ወረብ ጥናት ልምምድን ጎበኙ። Link to: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ ዶክተር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አስመልክቶ የሊቃውንት ወረብ ጥናት ልምምድን ጎበኙ። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ ዶክተር የቅዱስ... Link to: የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በመከበር ላይ ነው። Link to: የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በመከበር ላይ ነው። የ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top