ነሐሴ 10 ቀን 2017ዓ.ም
+ + +
፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት (ዶ/ር) 13ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ጠበቂ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨውና የራያ ስድስቱ ወረዳዎች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የማኅበራት ክትትልና ቁጥጥር ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኀላፊ፣( የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ተወካይ) ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስአበባ ፣ የሐድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ፣ ረ/ፕ ቀሲስ ግርማ ባቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢኮኖሚ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢ/ሃ ጉ/ጠ/ፀሐፊ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ የየመምሪያና የየድርጅት ኀላፊዎች ፣ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ፣ የቅዱስነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ፣ ምዕመናንና ምዕመናት በተገኙበት በጸሎተ ፍትሐት፣ በደማቅ መንፈሳዊ አገልግሎት የታሰበ ሲሆን።
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ “”ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዋኖቻችሁን አስቡ” (ዕብ 13÷7) በማለት ቅዱስነታቸው የሚያወሳ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የብፁዕ ወቅዱስ ተወካይ አባታዊ መልዕክት ተላልፎ በጸሎት ተዘግቷል።