የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም በመከናወን ላይ የሚገኘውን የልማት ሥራና የሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሂደትን ጎበኙ።

December 16, 2025

ታኅሣሥ ፯ቀን ፳፻ ፲ወ፰ዓ.ም
==================
ኦሮሚያ-ወንጪ
****
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን የግንባታ ሥራ ክንውን የደረሰበትን ደረጃ ለመመልከት በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በወንጪ ይፋዊ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ፣ አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
ብፁዕ አቡነ ሕርያቅስ የአዲስአበባና የሀድያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የከምባታ ሀላባና ጠምባሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙኀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደገለጹት ገዳሙ ጥንታዊና ታሪካዊ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከያወኑ መሆኑን ገልጸው ከሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ በተጨማሪ የአብነት ትምህርት ቤት፣ሰንበት ትምህርት ቤት፣ሰንበቴ ቤት፣ሙዚየምና ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ወደብ የሚገነባ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።አያይዘውም ቦታው የቱሪስት ፍሰት የሚበዛበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግም ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች እንደሚከናወኑ የጠቀሱት ሙሐዘ ጥበባት አጠቃላይ የግግባታ ሥራው በዘጠኝ ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል።

የገዳሙ አጠቃላይ የግንባታ ሥራን በተመለከተም በባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል።የቤተክርስቲያኑ ግንባታ ሥራ ኃይማኖትን፣ታሪክንና ባህልን መሰረት ያደረገ እንደሆነም በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተውጣጥተው የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችም ለዚህ የተቀደሰ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በዚሁ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላሐፉት መልዕክት የወንጪ ቂርቆስ ቤተክርስቲያንን ለማሰራት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መሆናቸውን ገልጸው ሀይማኖት፣ታሪክና ባህልን አስተሳስሮ ኢትዮጵያዊ አንድነትን በተግባር የሚሰብከውን ፕሮጀክት በማስተባበርና በመምራት ላደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አያይዘውም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወንጪን በመሳሰሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ውስጥ ጥንታዊያን ገዳማትና አድባራት ታድሰውና ታንጸው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በማድረግ በታሪክ ውስጥ የሚዘከር ሥራ እየሰሩ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር በጸሎቷ ታስባቸዋለች፣ ምስጋናዋንም ታቀርባለች ብለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።
  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያንን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸምን ለመጎብኘት ወደ ድሬዳዋ ተጓዙ።
  • ለብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በደምቢ ዶሎ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዋኖቻችሁን አስቡ”  (ዕብ 13÷7) Link to: “ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዋኖቻችሁን አስቡ”  (ዕብ 13÷7) “ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዋኖቻችሁን አስቡ” ... Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቦታዎች ለምታስገነባቸው ሁለገብ ሕንጻዎች ከአሸናፊ ኮንትራክተሮች ጋር የግንባታ ሥራ ስምምነት ተፈራረመች። Link to: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቦታዎች ለምታስገነባቸው ሁለገብ ሕንጻዎች ከአሸናፊ ኮንትራክተሮች ጋር የግንባታ ሥራ ስምምነት ተፈራረመች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top