የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቦታዎች ለምታስገነባቸው ሁለገብ ሕንጻዎች ከአሸናፊ ኮንትራክተሮች ጋር የግንባታ ሥራ ስምምነት ተፈራረመች።

January 13, 2026

ጥር ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ ዓ.ም
*****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱና ከመንግስት በተሰጧት ቦታዎች ላይ ሁለገብና ዘመናዊ ሕንጻዎችን በማስገንባት በአስቸኳይ አገልግሎት ላይ እንድታውል የቅዱስ ሲኖዶስምልአተ ጉባኤ በግንቦቱ ርክበ ካህና ወቅት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሶኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በመቀናጀት የሰጡትን ቆራጥ አመራር መነሻ በማድረግ በሚገነቡ ሕንጻዎች አጠቃላይ ይዘት፣ደረጃና ዝርዝር የሥራ ሁኔታዎች ላይ በባለሙያዎች አማካኝነት ጥናት ሲካሔድ ቆይቶ ሕንጻዎቹን ለመገንባት ይቻል ዘንድ ሕጋዊ ጨረታ እንዲወጣ ተደርጎ በዛሬው ዕለት ጨረታውን ካሸነፉ ኮንትራክተሮች ጋር አማካሪ ድርጆቱ EEF በተገኘበት የውል ስምምነት ፊርማ ሥነሥርዓት ተከናውኗል።

በዛሬው ዕለት የፊርማ ሥነሥርዓት ከተከናወነባቸው የግንባታ ሥራዎች መካከል ፒያሳ አካባቢ የሚገነባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዝክረ ቅዱሳን ህንጻ 2B G+7አንዱ ሲሆን የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ምንሀር ኮንስትራክሽን የተባለው ሕንጻ ተቋራጭ ሲሆን አራት ኪሎ አካባቢ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀርባ ባለው ስድስት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሕንጻ አበው በሚል ስያሜ ለሚገነባው 2B+SBG+12+T ሁለገብ ሕንጻ ደግሞ አተም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተባለው ድርጅተ አሸናፊ በመሆን ከቤተክርስቲያናችን ጋር የግንባታ ውል ስምምነት ተፈራርሟል።

ቤተክርስቲያን በሕንጻ ግንባታ ዘርፍ በርካታ አዳዲስና ዘመናዊ ሕንጻዎችን በመገንባት ለበርካታ ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድልን እንደምትፈጥር፣ከሕንጻ ኪራዩ በሚገኘው ገቢም መንፈሰዊ አገልግሎቷን እንደምታስፋፋና እንደምታጠናክር እንዲሁም በከተማችን የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግሮችንም በመፍታት ማኅበራዊ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ወቅት ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ብፁዕ አቡነ አቡነ ሳዊሮስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤተክርስቲያናችን ታሪክ የመጀመሪያና ግዙፍ የሆኑ ሕንጻዎችን መገንባት የሚያስችላትን ሰኬታማ ሥራ መስራት መቻልዎ ዕድለኝነትዎንና የልማት ሰውነትዎን የሚያረጋግጥ ስለሆነ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ካሉ በኋላ እነዚህን ታሪካዊ ሕንጻዎችን ለመገንባት ከቤተክርስቲያን ጋር ውል የገባችሁ ኮንትራክተሮችም የተጣለባችሁን ከባድ ታሪካዊና መንፈሳዊ ኃላፊነት በትጋትና በታማኝነት በመፈጸም ሥራችሁን በገባችሁት ውል መሰረት በስኬት እንድትወጡ አደራ ለማለት እንወዳለን ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ውል ተገብቶባቸው ወደ ሥራ የገቡት ሁለቱ ግዙፋን ሕንጻዎች በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያዎቹና በግዝፈትና በጥራታቸው የተዋጣላቸው ሆነው የሚገነቡ ሲሆን ለቤተክርስቲያናችን ኩራትን ለከተማችን ተጨማሪ ውበትን የሚያላብሱ ግንባታዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።ሕንጻዎቹ በአራት ኪሎ አካባቢ የሚገነባው በሰላሳ ወራት፣ ፒያሳ አካባቢ የሚገነባው ደግሞ በሃያ ወራት ውውጥ የሚጠናቀቁና አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሆናቸው ታውቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም በመከናወን ላይ የሚገኘውን የልማት ሥራና የሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሂደትን ጎበኙ። Link to: ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም በመከናወን ላይ የሚገኘውን የልማት ሥራና የሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ ሂደትን ጎበኙ። ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወንጪ ቅዱስ ቂርቆስ... Link to: የጃን ሜዳ ባሕረ ጥምቀት ለበዓሉ ዝግጁ እንዲሆን አስፈላጊው ሥራ እየተሠራ መሆኑን የበዓል ዝግጅት ኮሚቴው አሳወቀ። Link to: የጃን ሜዳ ባሕረ ጥምቀት ለበዓሉ ዝግጁ እንዲሆን አስፈላጊው ሥራ እየተሠራ መሆኑን የበዓል ዝግጅት ኮሚቴው አሳወቀ። የጃን ሜዳ ባሕረ ጥምቀት ለበዓሉ ዝግጁ እንዲሆን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top