“አባ ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉት በፈቃዳቸው ይቅርታ ጠየቁ እንጂ “ያፈነም” “ያስገደደም” አካል የለም ይህ የሐሰት ወሬ ነው ከዚህ ይልቅ በሕገወጥ መንገድ ያላችሁ አካላት በይቅርታ ወደ ቤታችሁ መመለሱ ይበጃል”
“አባ ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉት በፈቃዳቸው ይቅርታ ጠየቁ እንጂ “ያፈነም” “ያስገደደም” አካል የለም ይህ የሐሰት ወሬ ነው ከዚህ ይልቅ በሕገወጥ መንገድ ያላችሁ አካላት በይቅርታ ወደ ቤታችሁ መመለሱ ይበጃል”
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቀራራቢ ዐቢይ ኮሚቴ
በሕገ ወጥ “ሢመተ ኢጲስ ቆጶስ” ከተሳተፉ አካላት በይቅርታ የሚመለሱ አካላትን የሚያቀራርብ ዐቢይ ኮሚቴ በዛሬ ዕለት በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥቷል።
በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርግ መቆየቱን የገለጸው ኮሚቴው እዚህ ደረጃ ለመድረሱ አስተዋጽኦ ላደረጉ የበጎ ሐሳብ ባለቤቶች ምስጋናውን አቅርቧል።
የአቀራራቢ ኮሚቴው በይቅርታ እንዲመለሱ ካደረጋቸው መካከል አባ ፀጋ ዘአብ አዱኛ ተጠቀሽ ሲሆኑ በሌላ በኩል በፈቃዳቸው ይቅርታ የተጠየቁትና በኋላ ግን “ተገድጄ ነው” ያሉት “አባ” ንዋየ ሥላሴ የተባሉ ግለሰብ የተናገሩት ያልተደረገና የሐሰት ሥራ መሆኑ ኮሚቴው ገልጿል።
ከዚህ በማያያዝ በሕገወጥ መንገድ እየተጓዙ ላሉ አካላትም አሁንም የአቀራራቢ ኮሚቴው የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ እንደሚችል ጠቅሶ በይቅርታ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱም ጥሪ አስተላልፏል።