ሀገረ ስብከቱ የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ጥቅል የሥራ አፈጻጸም ውይይት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሐላፊ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሪነት መከናወኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ የተገኙ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የየክፍላት ኀላፊዎች በዓመቱ ውስጥ የነበረውን የክፍላት አፈጻጸም ጥቅል ሪፖርት አቅርበዋል።
በበጀት ዓመቱ ከነበረው ፈተና አንጻር በሀገረ ስብከቱ የነበረው አፈጻጸም በጣም ጥሩ እንደነበር ተነስቶ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ አዲስ ዘመን የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ የነበሩ ክፍተቶችን ሞልቶ መቀጠል እንደሚገባ ያመለከተ የሥራ መመሪያ እና አቅጣጫ በብፁዕነታቸው ተሰጥቷል ሲል የሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ዘግቧል።