የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

September 9, 2024

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዛሬው ዕለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

የተከበራችሁ የሃገራችን ሕዝቦች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ምዕመናን፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሀገርን ዳር ድንበር እና ሰላም ለማስከበር ቀን ከሌት የምትደክሙ የሠራዊት አባላት፣ በሕመም ምክንያት በቤታችሁ እና በሕክምና ማዕከላት የምትገኙ ሕሙማን፣ በማረሚያ ቤቶች የምትገኙ የሕግ ታራሚዎች በአጠቃላይ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓመተ ምሕረት የዘመን መለወጫ ባዕል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፣ አደረሰን፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ፈተናዎች ቢገጥሟትም በፈጣሪ እርዳታ እና በሕዝባችን አስተዋይነት እንዲሁም  ትጋት ለማለፍ ችላለች፡፡ ሰላም በአንድ ቀን በሚሠራ በጎ ሥራ የሚገነባና የሚጠናቀቅ ባልለመሆኑ ሁላችንም በሃገራችን አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፣ ከግጭት ይልቅ እርቅን፣ ከመለያየት ይልቅ አንድነትን፣ ለእኔ ብቻ ከሚል ክፉ አስተሳሰብ ለእኛ ማለትን፣ ከንቀት ይልቅ መከባበርን፣ ከልባችን በመምረጥ በአስተማማኝ ሰላሟ ተምሳሌት የሆነች እና ያደገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በቅን ልቦና እንድንሰራ በፈጣሪ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በተለይም በየደረጃው የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ፈጣሪ እና ሃገር የጣሉብንን ታላቅ ኃላፊነት እና አደራ ሰላምን በመስበክ እና በመጠበቅ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የተቸገሩትን በመርዳት እና  ፍትህ ላጡ እና ለተበደሉ ወገኖቻችን ድምጽ በመሆን ከምን ጊዜውም በላይ እንድንሰራ አደራ ለማለት እንወዳለን፡፡

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የምሕረት፣ የርህራሄና፣ የአንድነት እና የመረዳዳት ዓመት እንዲሆንልን በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስም እየተመኘን በዓሉን ስናከብር በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህል የተቸገሩትን በመርዳት እና በአዲሱ ዓመት በሃገራችን የተሟላ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቃል በመግባት እንዲሆን በፈጣሪ ስም አደራ ለማለት እንወዳለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/yehaymanot-tequamat.jpg 430 657 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2024-09-09 14:01:152024-09-09 14:02:05የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
  • ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ተመለከቱ፤ በድሬዳዋ መልካ ጀብዱ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የሚገኙ እጓለማውታ ሕጻናትን ጎበኙ።
  • የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያስገኘባው ባለ ሦስት ወለል ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ በዛሬው ዕለት ተመረቋል።
  • የቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ተባረከ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጓዘ።

Archives

  • July 2026
  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: “ለቤተክርስቲያን አይደለም ጥቅማጥቅማችንን አንገታችን እንሰጣለን” ብፀዕ አቡነ አብርሃም Link to: “ለቤተክርስቲያን አይደለም ጥቅማጥቅማችንን አንገታችን እንሰጣለን” ብፀዕ አቡነ አብርሃም “ለቤተክርስቲያን አይደለም ጥቅማጥቅማችንን... Link to: የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አደረገ። Link to: የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አደረገ። የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የበጀት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top