የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና ማስተባበሪያ መምሪያ
የመምሪያው ተልዕኮ፡-
- በኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያበየደረጃው በተዋቀሩ የመምሪው ተቋማት ለሚታቀፋ ሕጻናት ፣ወጣቶችና ጎልማሶች ፣በትምህርተ ሃይማኖት፣ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያና በዓለም የክርስትና ታሪክ በቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤቶች በቤተክርስቲያ አገልግሎት ምሥጡራዊ አፈጻጸም በተቀደሰ ትውፊት ላይ ወጥነትና ተከታታይነት ያለው እውቀትን ማስተላለፍ፤
- ለሕጻናት ለወጣቶች የሚሰጠው ትምህርት አሰጣጡ በአደረጃጀቱ ና በዘዴው ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ እየተሸሻለ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ተልዕኮና የማደራጀት መምሪያውን ራዕይ የሚሳካ በሚሆንበት መልኩ የተቃኘ ማድረግ ማድረግና መቁጣጠር፤
- ወጣቶች ከቤተ ክርስቲያኗቷ ትምህርት ሥርርዓትና የክርስቲያናዊ ማንነት መገለጫ ከሆኑት ማኅበራዊ መስተጋብርና አኗኗር፣ ጠባይና ሥነ ምግባር የሚያስወጡ የየዘመናቱን ኢ-ክርስቲያናዊ ለውጦች በመከታተል በክርስቲያናዊ ትምህርት ፣መታገልና ወጣቶችን ከመነጠቅ መጠበቅ እንዲሁም ይህንን ተጋድሎ ማስጠበቅ የሚችልና ለመጭው ትውልድ ጽኑ የሆነ ተቋማዊ መሠረት መጣሉን ማረጋረጥ፤
- ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት ፣ከክርስቲያናዊ ወላጆች ትውፊት ፣ከማኅበረሰቡ ኢትዮጵያ የክርስትና አኗኗርና ፍስፍና ወጣቶችና የሚመጥንና ክርስቲያናዊ ማንነትን የሚያስጠብቅ አዳዲስ ስልቶችንና ዘዴዎችንበመዘርጋት ክርስቲያዊ የሚመጥንና ክርስቲያናዊ ማንነት ከጥፋት መታደግ፤
የማደራጃ መምሪያው እሴቶች፡-
- በቅድስና ስምሳሌ የሆነ አስተዳደራዊ አገልግሎት፡- ተቋማዊ አገልግሎት በይዘት በአኗኗርና በድርጊት ቅድስናን የሚመሰከር ለሕጻናትና ወጣቶች እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ በማለት አምላካችን ያዘዘንን ትዕዛዝ የሚተረጉም መሆን የሚረጋገጥ፤
- ጽናትና ምስክርነት፡- በጊዜውም በክርስቲያናዊ ማንነት መጽናትን በተግባር የሚተረጉምና የተጋድሎ ምሳሌ የሆነ ውሳኔ አገልግሎትና ተግባራዊ ምስክርነት፤
- በርቅር የሆነ አገልግት፡- በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ለማጽናት የሌሉትን በትህርትና በኑሮ ምሳሌነት ለማምጣት እየተጉ ለሁሉም ፍቅርን መስጠት፤
- ዘመኑን መቅደም ፡- ክርስቲያ ወጣቶች ኢ-ክርስቲያናዊ እሴቶች ላይ ነገር ግን በዘመናዊ ቴክኖጂ የመረዳት እየተፋፋመ በሚገኘው ሉላዊነት አንጻር ዓለሙን ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ የሚለውን የክርስቲያናዊ ሉላዊነት አማላካዊ ትዕዛዝ በሚፈጽሙት ላይ የተቀደነቀውን የክርስቲኖችን ፈተናዎች የመቋቋሚያ አቅም እንዲያዳብሩ ማስቻል፡፡
- ክርስቲያናዊ ኃላፊነት፡- የወጣቶች ሕይወት ከእውነትን መንገድ የወጣ እንዳይሆን ፍጹም በሆነ ትጋት ቁጥጥር በማድረግ የመልካም ሥነ ምግባር የታታሪነት የሀገርና የሰው ልጆች ፍቅር ምሳሌ መሆን፡፡