መስከረም 19/1/2017
ባሕር ዳር ሀ/ስብከት፦
1ኛ ክፍል
2ኛ ክፍል
3ኛ ክፍል
7ኛ ክፍል
አዲሱን ሥርዓተ- ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ 6,675ተማሪዎችን አስመረቀ።
በዚሁ የተማሪዎች ምርቃት ስነ-ሥርዓት ላይ የሀ/ስብከቱ ዋና ፀሐፊ እና የዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይ መልአከ ብርሃን ፍስሐ ጥላሁን እና የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።
በዚህ ሥርዓተ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ይማሩ የነበሩ የደረጃ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ሽልማት ተሰጥቶአቸዋል።
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ አጠቃላይ የመማር ማስተማሩን ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ መፍትሔዎችን ያካተተ ሪፓርት አቅርበዋል።
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ አቶ አየለ የሰልጣኞች ስልጠና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰልጥነው የመጡት ሰልጣኞች ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መመሪያ በመስጠትና ክትትል በማድረግ ዛሬ በ 41 የሰንበት ትምህርት ቤቶች ትምህርቱን በደንብ የተከታተሉና የመመዘኛ ፈተና ተፈትነው ያለፉትን ተማሪዎች ሰናስመርቅ ብፁዕ አባታችን ላደረጉልን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።
በመጨረሻም በሀ/ስብከቱ ጸሐፊ እና የዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይ እና በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ መርሐ-ግብሩ በጸሎት ተዘግቶ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል ።
መረጃው የሀገረ ስብከቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው