መጋቢት 26ቀን 2016ዓ.ም
**
ቄለም ወለጋ
“”””””””””””
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት (26/07/2016) ሐዋርያዊና መንፈሳዊ ጉዞአቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ደምቢ ዶሎ በማድረግ ላይ እንዳሉ በዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጫሞ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ብፁዕነታቸውም፦
– ለተሰበሰቡት ምዕመናን አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ስጥተዋል።
– ለቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ የሚሆን 20000 ብር ድጋፍ አድርጎዋል።
– ለደብሩ ሰንበት ት/ቤት የሚሆን መሉ የደምብ ልብስ በነፃ ሰጥተዋል።
– ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ ልብሰ ተክህኖ በነፃ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸውም በመጨረሻ ወደ ደምቢ ዶሎ ከተማ ሲደርሱ በሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና በከተማው ማህበረ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው መንበረ ጵጵስናቸውን በሰላም ገብተዋል።ሲል የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ልጿል።