የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የደምቢ ደሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራልን ቅዳሴ ቤት አከበሩ።

April 6, 2024

መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
===================
ደምቢዶሎ ኢትዮጵያ
*****
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል  የቄለም ወለጋ፣ የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን፣ የቤ/ጉሙዝ አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የሰላምና የልማት አምባሳደር  በዛሬው ዕለት በ27/07/2016 በደምቢ ዶሎ ደ/ጸሐይ መድኃኔዓለም ካቴድራል በመገኘት የታደሰውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመባረክ፣ ቅዳሴ ቤቱን አክብረዋል።

ብፁዕነታቸው በዚሁ ጊዜ ዕለቱን በተመለከተ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በመስጠት አባታዊ  ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል።ለቤተ ክርስቲያኑ የልማት ሥራ የሚህን የ100.000 (አንድ መቶ ሽህ) ብር ድጋፍ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ለካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት የደምብ ልብስ ስጦታ አበርክተዋል በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሆን ልብሰ ተክህኖም  አበርክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ከሁለት ኩንታል በላይ  በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መልዕክት የታተመበት ቲሸርት በበዓሉ ላይ ለተገኙ ምዕመናንና ምዕመናት በስጦታ ማበርከታቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል ለአገልጋዮች የሚሆን በአባ ገዳ የተሰራ ሃያ ነጠላ ያበረከቱት ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ የገጠማትን ፈተና በሚገባ በመወጣት በእግዝአብሔር አጋዥነት ችግሩን እናልፈዋለንና በርቱ በሐይማኖታችሁ ጽኑ በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

ብፁዕነታቸው  በትላንትናው እለት በ26/07/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ከአዲስ አበባ በ ወደ ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ደምቢ ዶሎ በመጓዝ  በዳሌ ሰዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ጫሞ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበሉ ወቅት ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስጠታቸውን፣ ለህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ የሚሆን 20.000.00 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን፣ለደብሩ ሰንበት ት/ቤት የሚሆን መሉ የደምብ ልብስ መለገሳቸውን፣ደምቢ ዶሎ ከተማ ሲደርሱም በሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና በከተማው ማህበረ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን  የሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን ዘገባ ጨምሮ ገልጾልናል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሐዋርያዊ ጉዞ Link to: የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሐዋርያዊ ጉዞ የብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሐዋርያዊ ጉዞ Link to: ኦርቶዶክሳውያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን Link to: ኦርቶዶክሳውያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳውያን ብዙኀን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top