የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ዙሪያ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቶ ባለ ፮ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
ጥር ፲፱ ቀን ፳፻ ወ፭ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በትላንትናው ዕለት የቤተክርስቲያናችንን ዶግማ፣ቀኖናና አስተዳደራዊ ሥርዓትን በመጣስ በክህደት የተሰጠውን ሲመተ ጵጵስና አስመልክቶ ውሳኔ ማክተላለፉ ይታወሳል።
ይህንን መሰረት በማድረግም የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣የክፍላተ ከተማ ሊቃነ ካህናትና ሰራተኞቻቸው፣የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት በተገኙበት ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ታሪካዊ ውሳኔ ዙሪያ ውይይት ካደረጉ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፤