ነሐሴ ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመሪ እቅድ መምሪያ ያዘጋጀው የ፲ ዓመት መንፈሳዊና ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በእግዚአብሔር ኃይል ጠንካራና ሁለገብ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንተጋለን ! በሚል ርዕስ ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ምክትል ሊቃነ መናብርት በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ሁለገብ አዳራሽ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም. ከጠዋቱ ፫ ሰዓት ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ውይይትና ምክክር እየተከናወነ ነው፡፡

በመሪ ዕቅድ መምሪያ በተዘጋጀውና ለአንድ ቀን በሚቆየው የሥልጠና መክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በመሪ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ በንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ ገለጻ ተደረጓል ፣በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሪ ዕቅድ አስፈላጊነት፣በተቋማዊ አሰራር መተግበርና በሚያስገኘው ውጤት ዙሪያ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሰፊ ትምህርት፣ ቃለ በረከትና ቡረኬ ከሰጡ በኋላ የጉባኤውን መከፈት አብስረዋል ሲሉ::ፎቶግራፍና የዜና መነሻ ጽሑፍ ያደረሱን መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ ገልጸዋል።