በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሰሜንና ምሥራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ በችግር ሰዓት የቆመ ጣቢያ መሆኑን ጠቅሰው በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደብዳቤ መነሻነት ለተራዱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር) የኢኦቴቤ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው “ድርጅታችን የምሥረታ ጊዜውን አጠናቆ ተቋማዊ ቅርጽ ይዟል።

በሀገር ውስጥና ውጭ ካሉ ምእመናን ከ160 ሺህ ዶላር በላይ በመሰብሰብ የቀጥታ ሥርጭት መሳሪያ ገዝተው ግዴታቸውን ተወጥተዋል። በዚህም በመንፈሳዊ ልጆቻችን ኮርተናል”ብለዋል።

ለመሰረታዊ ለውጥ ጥናት እየተደረገ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ ድርጅቱ የራሱን ሕንጻ መገንባት፣ የቋንቋ ተደራሽነት ማስፋት፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግና በጠንካራ ይዘት መስራት ትኩረት እንደሚሰጧቸው ገልጸዋል።