ጥር ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፰ዓ.ም
++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””‘”””””””””””””””
የ፳፻፲ወ፰ ዓ/ም የከተራ እና ጥምቀትን በዓላትን ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። የበዓሉን ዝግጅት የዓመቱ ተረኛ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ጋር እንዲሁም ለበዓሉ ከተመደበው ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
የቅድመ ዝግጅት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ለመጎብኘት ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ/የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣መምህሬ ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ቴሌቪዥን ሥርጭት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የመምሪያ ኃላፊዎች እና የደብሩ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የተጀመረው የቅድመ ዝግት ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በምክትል ሥራ አስኪያጁ መመሪያ ተሰጥቷል።






