ጥር ፲፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””
ባህርዳር -ኢትዮጵያ
+++++++++++
ብፁዕ አብነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና አቶ ጎቩ እንዳላማው የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ክቡር መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሰኪያጅ፣ መ/ገ አምደ ሃይማኖት የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በባሕርዳር ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተከበሮ ውሏል።
በትናትናው ዕለት በአንድ ላይ ወደ ጥምቀተ ባህር የወረዱት ታቦታት በቁጥር 32 ሲሆኑ በዛሬው ዕለት 28 የሚሆኑት ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው በሰላም ተመልሰዋል። ቀሪዎቹ 4 ታቦታት በነገው እለት ወደ መንበረ ክብራቸው የሚመለሱ ይሆናል።
ብፁዕነታቸው በዚሁ በዓል ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት በዚህ በዓል ላይ የተገኘን ሁሉ በዚህ መልኩ አምረንና ተውበን የተገኘነው ሃይማኖታችን ጠርቶ ንነው ካሉ በኋላ በዓሉን እያከበርነው ያለው ቤተ ክርስቲያን የሰላም የፍቅር ፣የአንድነት መገለጫ ስለሆነች ነው ብለዋል አያይዘውም በዚህ በዓል ሁላችንም በመተሳሰብና በመደጋገፍ እናክብር በማለት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕነታቸው ሁሉንም ታቦታት በአንድነት እስከ ዲፖ ድረስ ከሸኙ በኋላ ታቦተ ጊዮርጊስን አጅበውና አክብረው ወደ መንበረ ክብሩ የመለሱ ሲሆን በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በቃለ ምእዳንና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።
ዜናውን ያደረሱን መምህር ጥበቡ ክበር የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ናቸው።