ሚያዚያ ፲ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
“”””””””””””””””””””

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያና የየድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች ክቡር ሊቀ አእላፍ በላይ ጸጋዬ የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፣የአድባራትና ገዳማት ከስተዳዳሪዎች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉን በማስመልከት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማትን በመወከል መልዕክት የቀረበ ሲሆን ቅኔዎችም በሊቃውን ቀርቧል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም በአሉን በማስመልከት የእንኳን አደረሰዎ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው ቤተክርስቲያን በውስጥና በውጪ የገጠማትን ፈተና ለመቋቋም ቅዱስነትዎ የሰጡት ትዕግስትና ብልሀት የተሞላበት አመራር የሚደነቅ ነው።
ብለዋል ። አያይዘውም አሁን ያለነወ አባቶች አንዲት ቤተክርስቲያን ፣አንድ ሲኖዶስ፣አንድ ፓትርያሪክ የሚለውን ክስስቲያናዊ መርህን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንችል ዘንድ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንድንወጣ አደራ እላለሁ ብለዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅትም በዕለተቱ ለቅዱስነታቸው ሥጦታ ያበረከተ ሲሆን ድርጅቱ “ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር” በሚል መሪ ቃል፦
እንደአባቶቻችን ብራና ዳምጦ፣ብዕር ቀርጾ፣ ቀለም በጥብጦ፣የተለያዩ ማዕድናት አቅልጦ፣ ትውፌታቸውን የጠበቁ የብራና መጻሕፍቶችን ፣የብራና አና የገበቴ(የእንጨት) ቅዱሳት ስዕላትን፣የተለያዩ ንዋያተ ቅድሳቶችን ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ያመርታል።

ድርጅቱ እስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ የብራና መጻሕፍቶችን እና ቅዱሳት ስዕላቶችን በማምረት ለገዳማት፣ ለአድባራት፤ለአብያተ ጉባኤያት ና ለምዕመናን ከማቅረባቸውም ባሻገር ይህን የቀደምት ኢትዮጰያውያን አባቶቻችን ጥበብ ለትውልዱ እንዲተላለፍ የተለያዩ የስልጠና ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ዛሬም ይህንን በተቋማቸው የተዘጋጀውን በውስጡ ፭ ስዕላት፣፭ ሐረጋት ያካተተ የ ፬ቱ ወንጌላውያን የብራና ወርቅ ወንጌል የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት ለብዑዕ ወቅዱስ አቡነ ምትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አበርክተዋል።በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ቃለ በረከትና ቃለ ቡራኬ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።