ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻ ፲ ወ ፮ዓ.ም
“”””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******

፵፪ ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ነገ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም ይጀመራል።

ጉባኤው ከመላው ዓለም የሚመጡ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት ሲሆን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትን የ፳፻ ፲ ወ ፭ ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምን የሚያቀርቡ ሲሆን የሁሉም አህጉረ ስብከት ሪፖርት በንባብ ይሰማል ጉባኤውም በተመረጡ የመወያያ ርዕሶችና በምልዓት በሚነሱ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለአምስት ቀናት ይካሔዳል።

በጉባኤው በሪፖርትና በውይይት የሚነሱ ሀሳቦችን መሰረት ያደረገ የአቋም መግለጫ የሚቀርብ ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኘፈኤ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሲጸድቅ የ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም የሥራ መመሪያ ሆኖ ለማዕከልና ለአህጉረ ስብከት ይተላለፋል።

በነገው ዕለት የሚካሔደውን ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን ለማካሔድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሁሉ በሚገባ የተጠናቀቁ ሲሆን ጉባኤተኞችም አስቀድመው በመግባት የጉባኤውን መጀመር እየተጠባበቁ ይገኛሉ።ጉባኤው ስኬታማና ውጤታማ እንደሚሆን ይጠበቃል።