የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ሕግና ደንብ የሚመራ “ፍኖተ ጽድቅ ብሮድካስት አገልግሎት” የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊከፈት ነው።

October 15, 2023

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻ ፲ ወ ፮ ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ሕግና ደንብ የሚመራ “ፍኖተ ጽድቅ ብሮድካስት አገልግሎት ” የተሰኘ የቴሌቪዥን ድርጅት ሊያቋቁም ነው።

ድርጅቱ የሚያቋቁመው ዘመናዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተዳደርበት ደንብና የሚዲያ ሥራውን የሚያከናውንበት ኤዲቶሪያል ፓሊሲ የቤተ ክርስቲያናችንን ዶግማ፣ቀኖና፣ሕግና መመሪያን መሠረት ያደረገ ሆኖ መዘጋጀት ይችል ዘንድ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ከታዋቂ ሰባኪያን፣ከታላላቅ የአገራችን የቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል።

በዚሁ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብና ኤዲቶሪያል ፓሊሲ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ በስራ ላይ የሚውል ሲሆን ፍኖተ ጽድ ብሮድካስት አገልግሎትም ደንብና መመሪያዎችን አክብሮ የመስራት ግዴታ ይኖርበታል።

ተዘጋጅተው የቀረቡት የማቋቋሚያ ደንብ እና ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ፍኖተ ጽድቅ የብሮድካስት አገልግሎት የበቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ብቻ ማእከል አደርጎና በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ታቅፎ እንዲያገለግል የሚደረግ ከመሆኑም በላይ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የፍኖተ ጽድቅ የብሮድካስት አገልግሎትን መከታተል፣ መቆጣጠር ፣ ማገድና መሰረዝ የሚያስችሏትን መብት የሚሰጣት ነው ።

በባለሙያዎቹ ተጠንቶ የተዘጋጀው ኤዲቶሪያል ፖሊሲ በፍኖተ ጽድቅ በሚዘመሩ መዝሙራት እና የመዝሙር መሣሪያዎች ላይ የሚታዩ አንዳንድ ክፍተቶችን የሚያርም ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላም ለአገልግሎት የሚውሉ መዝሙራትና የመዝሙር መሣሪያዎች በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተፈቀዱ ብቻ መሆን እንደሚገባቸው መደንገጉን ከፖሊስው መረዳት ተችሏል።

በትላንትናው ዕለት በሀርሞኒ ሆቴል በተፈጸመው የማቋቋሚያ ደንብ እና ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሰነድ ርክብክብ ላይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ የምሥራቅ ሽዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ፣ የቤተመጻሕፍት ወመዘክርና የማኅበራት ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ኢሉ አባቡራ፣ቡኖ በደሌና በሰሜን አሜሪካ የሜኒሶታና አካባቢው አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የኢትዮጵያ ሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የጠቅላይ ባቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣የማኅበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ጊዜም በረቂቅ ማቋቋሚያ ደንቡና በኤዲቶሪያል ሰነድ ዝግጅት ላይ ለተሳተፉ ባለሙያዎችና የበኩላቸውን ድጋፍና ትብብር ላደረጉ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ረቂቅ ሰነዱ በ”ፍኖተ ጽድቅ” በበይነ መረብ ሚዲያ ይተላለፉ የነበሩ ክፍተቶችን አርሞ ከማስቀጠልና በቤተ ክርስቲያናችንም ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሰነድ እንደሆነም ተገልጿል። በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከዚህ በኋላ የፍኖተ ጽድቅ ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ነው ብለዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፍ/ደ/መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅ/አርሴማ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤትለሚያሳንጸው ሕንጻ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። Link to: ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፍ/ደ/መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅ/አርሴማ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤትለሚያሳንጸው ሕንጻ ቤተክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ... Link to: የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ። Link to: የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ። የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top