ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
******
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
******
የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ፵፪ኛውን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን አካሔደ።የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባዔው ከመካሔዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎም በሀገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ታላቅ ጉባኤ መካሔዱን ከሀገረ ስብከቱ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

በጎንደር ከተማ ከህዳር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲፮ዓ.ም በተካሔደው ታላቅ ጉባኤ ላይ የሁሉም ምስክርቤት መምህራን፣ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሀዲስ አራት አይና፣ ቆሞስ አባ ገ/ማርያም ፣መጋቤ አዕላፍ ክቡር ጥላሁን ፣መጋቤ ሀዲስ ቃለህይወት በዛ ፣መጋቤ ምስጢር ነቃጥበብ እሸቴ፣ የጎንደር አብነት መምህራን ተወካዮች፣ የተገኙ ሲሆን ኅዳር ፲፱ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም በቸካሔደው ፵፪ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ገጉባኤ ላይም ከ ፳፯ ወረዳ የተወከሉ ሊቃነ ካህናትና የሥራ ኃላፊዎች የርዕሰ ከተማው ጎንደር ፵፭ አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች ፣ሰባክያነ ወንጌል ፣ማህበረ ቅዱሳን፣የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት እና የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

ጉባኤው በብጹዕ አቡነ ዮሐንስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ርዕሰ መንበርነት፣ በክቡር በኩረ ትጉኃንዘርዓ ዳዊት የሀገረስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መሪነት የተካሔደ ሲሆን
*ስለቤተክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነት
*ስለሀገር ሰላም
*ስለስብከተወንጌልና አብነት ትምህርት ቤቶች
*ስለካህናትና ምዕመና አኗኗር ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጓል ።

በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መልአከ መዊዕ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትምህርትና ስልጠና መምርያ ኃላፊ ተገኝተው “የቤተክርስቲያናችንን ወቅታዊ ፈተናዎች የሚመክት አገልጋይ ማዘጋጀት “በሚል ርዕሰ ሰፋ ያለ ጥናታዊ ጽሑፍ በማዘጋጀትና በማቅረብ ጉባኤው በተሰጠው ትምህርት አማካኝነት ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኝ ያደረጉ ከመሆኑም በላይ ለዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ ድምቀት ሆነው መዋላቸውን ሀገረስብከቱ ገልጾ በበጀት ዓመቱ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ ወረዳዎች በሀገረ ስብከቱ ቷኩል የተዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተሰጥቶ ጉባኤው መጠናቀቁን ሀገረ ስብከቱ በላከልን መረጃ ገልጿል።