የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት መሆኑን በመገንዘብ ሕግና መመሪያን አክብሮ እውነትና እውነተኝነትን መርሁ አድርጎ እንዲሰራ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ።

November 28, 2023

ኅዳር ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
“””””””””””””””””””””””””””
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ለመፍታትና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት በዛሬው እለት ባደረጉት የጋራ ጉባኤ ተስማሙ።

ሀገረ ስብከቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት በይግባኝ የቀረቡ አቤቱታዎችና ለጉባኤው በአጀንዳነት የቀረቡት ሰነዶች  በሸኚ ደብዳቤ እንዲደርሰው ተደርጎ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ እንደሚሰጥበት እንደሚያደርጉ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገለጹ።

በዚሁ የጋራ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብና ጥብቅ የሥራ መመሪያ ከእንግዲህ በኋላ በሀገረ ስብከቱ የአሰራር ስህተትና መመሪያን አክብሮ ባለመስራት ምክንያት የሚያለቅሱ ካህናት እምባቸው እንዲታበስ፣ማንም ሰው አያልቅስ፣ፍትህ እንዲነግስ፣የተበደለ እንዲካስ፣ቤተክርስቲያንን ብቻ ማዕከል በማድረግ እንስራ ፣የሚደረግ ዝውውርና የሚሰጥ ሹመት በህግና በመመሪያ ብቻ እንዲከናወን፣
የማንኛውም የሥራ ኃላፊና የአድባራት ወገዳማት አክተዳዳሪዎች ዝውውር ሥራን ማዕከል ባደረገ አግባብ ብቻ እንዲከናወን፣የሚከናወኑ ዝውውሮች ሁሉ በምክንያት ብቻ እንዲሆኑ፣ማንም ሰው ሲያድግም ሆነ ሲዛወር በሥራ አፈጻጸሙ ማለትም የሚያድግ ባሳየው የሥራ እድገት፣የሚዘወርድ ደግሞ ባስመዘገበው የሥራ ድክመት ብቻ እንዲሆን፣በተደጋጋሚ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ በተሰጠው መመሪያ መሰረት ከሥራ ገበታቸው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጅ አገልጋዮች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ ወደ ሥራ መደባቸው እንዲመለሱ የመጨረሻና ጥብቅ መመሪያ ሰጥተዋል።

በሀገረ ስብከቱ በኩል ከጠቅላይ ቤተክህነት የሚሰጡ መመሪያዎችን ሁሉ “ጠቅላይ ቤተክህነት ምን አገባው” በሚል ሰንካላ ምክንያት የሚደረገው መመሪያን ያለማክበርና ያለመፈጸም ተግባር  ችግሮችን ላለማባባስ ሲባል በትዕግስት ስናልፈው ቆይተናል ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከዚህ በኋላ ይህ አይነቱ ተግባር ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና በትዕግስት የምናልፈው ጉዳይ አይደለም  ብለዋል።

አያይዘውም ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መመሪያ መሰረት ሀገረ ስብከቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ መሆኑን ታሳቢ ባደረገ አግባብ ሕግና ሕጋዊ አሰራርን ብቻ በመከተል ሥራውን ማከናወን እንደሚገባው ገልጸው በጅምላና ምክንያታዊ ባልሆነ አግባብ የሚደረግን ዝውውርና እድገት ጠቅላይ ቤተክህነቱ በፍጹም የማይታገሰው መሆኑን በመረዳት ሀገረ ስብከቱ ሕግን አክብሮ መስራት ይገባዋል ብለዋል።

በሀገረ ስብከቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር በብፁዕ አቡነ አብርሃምና በብፁዕ አቡነ ሔኖክ መካከል የተፈጠረ ችግር በመኖሩ የተፈጠረ  በማስመሰል ለህገወጥ ድርጊቶች ሽፋን ለመስጠት መሞከር ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በእርሳቸውና በብፁዕ አቡነ ሔኖክ መካከል ምንም አይነት ልዩነትና ጸብ የሌለ መሆኑን ጠቁመው እየተጋጨ ያለው ሥራው በህግና በመመሪያ ተደግፎ ማዕከላዊነትን ባልጠበቀ አግባብ በመከናወኑ ስለሆነ መፍትሔውም ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ደንብ አክብሮ መስራት ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

የምንሰራው ሥራ መንፈሳዊ አገልግሎት እንደመሆኑ መጠን እውነትንና እውነተኛነትን ብቻ መሰረት ባደረገ አግባብ መከናወን ይኖርበታል ያሉት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምዕመናንን ከሚያሳዝንና በቤተክርስቲያን ላይ አመኔታን ከሚያሳጣ ሥራ በመራቅ ሀቅን መሰረት አድርጎ መመሪያን በማክበር እንዲሰራ የመጨረሻ ያሉትን መመሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ጉባኤው እንዲህ አይነቱ የጋራ መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማሳሰብና በብፁ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የተሰጡ መመሪያዎችን አክብሮና አስከብሮ ለመስራት በመስማማት የዕለቱን ጉባኤ በጸሎት አጠናቋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን ልዑክ አርሲ-አቦምሳ ወረዳ ተገኝቶ ምዕመናንን አጽናና ጊዜያዊ ርዳታም አበረከተ።
  • “በአርሲ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን” የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
  • ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በሀገረ ስብከቱ ለካህናት የሚሰጠውን ሥልጠና በጸሎትና በቡራኬ አስጀመሩ።
  • ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።
  • በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው የሚመራ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

Archives

  • June 2026
  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባዔ አባላት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባዔ በማድረግ ላይ ናቸው። Link to: የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባዔ አባላት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባዔ በማድረግ ላይ ናቸው። የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት... Link to: ፵፪ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተካሔደ። Link to: ፵፪ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ተካሔደ። ፵፪ኛው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በማዕከላዊ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top