የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • መሠረታዊ መረጃዎች
      • ርእይ፣ ተልእኮ እና እሴቶች
      • ታሪክ
      • የአደባባይ በዓላት
      • ህግጋት
    • መዋቅር
      • ቅዱስ ሲኖዶስ
      • ሊቃነ ጳጳሳት
      • መምሪያዎች
      • አህጉረ ስብከት
      • ትምህርት ቤቶች
  • አስተምህሮ
    • አእማደ ምሥጢር
      • ምሥጢረ ሥላሴ
      • ምሥጢረ ስጋዌ
      • ምሥጢረ ጥምቀት
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን
    • ምሥጢራተ ቤተክርስትያን
      • ምሥጢር ጥምቀት
      • ምሥጢረ ሜሮን
      • ምሥጢረ ቁርባን
      • ምሥጢረ ንስሐ
      • ምሥጢረ ተክሊል
      • ምሥጢረ ክህነት
      • ምሥጢረ ቀንዲል
    • ልዩ ልዩ
      • ነገረ ድኅነት
      • ነገረ ማርያም
      • ነገረ ቅዱሳን
      • ነገረ መስቀል
      • ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
  • አገልግሎቶች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ማኅበራዊ አገልግሎት
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ምግባረ ሰናይ
  • መካናት
    • ቅዱሳት መካናት
      • አክሱም ጽዮን
      • ላሊበላ
      • ደብረ ሊባኖስ
      • ማውጫ
    • ቤተ መዛክርት
      • መንበረ ጸባዖት ቅ/ሥላሴ ቤተ መዘክር
      • የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገስት በአታ ለማርያም ቤተ መዘክር
      • ማውጫ
    • የጉብኝት መረጃዎች
      • የጉዞ መረጃዎች
      • የሚጠበቅ ሥርዓት
  • ያግኙን
  • English Site
  • Menu Menu

የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባዔ አባላት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባዔ በማድረግ ላይ ናቸው።

November 28, 2023

ኅዳር ፲፰ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
=================
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
“””””””””””””””””””””

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ጋር በሁለትዮሽ የአሰራር ሒደት፣በመልካም አስተዳደር፣በሕግ ፣ደንቦችና መመሪያዎች አከባበር በአጠቃላይ ሥራዎችን በተቋማዊ አሰራር ሒደት በማከናወን ዙሪያ የጋራ መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት እንዲደረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ዛሬ ኅዳር ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባኤ በማካሔድ ላይ ናቸው።

በጉባኤው መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት፣ቃለ በረከትና ቡራኬ በቤተክርስቲያናችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ሁላችንም እናውቀዋለን።ማስተካከልም እንችላለን ብለዋል።

እኛ በቤተክርስቲያናችን የሚስተዋለውን ችግር ለማስተካከል የምንቸገረው ልባችን ስላልተስተካከለ ነው።ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ራሳችንን ሳናስተካክል ሌላውን ማስተካከል ስለማንችል ቅድሚያ ራሳችንን ለማስተካከል ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል ብለዋል።

አያይዘውም ሁላችንም የቆምነው ለቤተክርስቲያናችን እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም።ያሉት ቅዱስነታቸው ችግሮቻችንን ለመፍታት መወያየት ተገቢ ነው።”ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም” እንደሚባለው ሁሉ ችግሮቻችንን ለመፍታት ከልብ ከተነሳን የሚያስቸግር ነገር ይኖራል ብለን እናምናለን ካሉ በኋላ ከተጠያቂነትና ከተወቃሽነት ለመዳን፣ቤታችንን ለማቅናትና ለማስተካከል የሚጎለን ምንድነው ?ያሉት ቅዱስነታቸው ይህን ለማድረግና ቤተክርስቲያናችንን ለመጠበቅ ሙሉ ሥልጣንና ኃላፊነት እያለን መቸገራችን ያስገርማል ብለዋል።

ዘወትር ሁላችንም ራሳችንን መመርመር አለብን የት ነው ያለነው፣ምንድነው የምንሰራው፣ወዴት ነው የምንሔደው ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ያለፈውን ጊዜ ችግሮች ማሰብና በተሰጠን መንፈሳዊ ኃላፊነት ልክ በመስራት ቤተክርስቲያንን መጠበቅና ምዕመናንን የሚያረካ ተግባር መፈጸም ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው ሁላችንም ራሳችንን በአግባቡ በመመርመር ራሳችንን እናስተካክል ካሉ በኃላ በአንድነትና በጽናት ለቤተክርስቲያናችን እንቁም።በመመካከር አንድ ሆነን በመቆም ለቤተክርስቲያን ህልውና በጋራ እንስራ እኛ ተመካሪዎች አይደለንም መካሪዎች እንጂ ስለዚህ መመካከር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚጠቅም ስለሆነ ተመካክረን እንስራ ችግሮችንም በግልጽ በማውጣት ለችግሮቻችን መፍትሔ በማበጀት ለውጤት ልናበቃው ይገባል በማለት አባታዊ መልእክታቸውን በማጠናቀቅ ጉባኤውን በይፋ ከፍተዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፦ መልካም አስተዳደርን ለማምጣትና ችግሮችን ለመፍታት ውይይት ወሳኝ ነው።ቅዱስነትዎም በቤተክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የዘወትር ምኞትዎና ጸሎትዎ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ ጊዜ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ተወያይተን መፍታትና የቁጥጥር ሥርዓታችንን በማጥበቅ ችግሮችን በአግባቡ መፍታት አለብን ብለዋል አያይዘውም ህገወጥ ቅጥርና ዝውውርን በተመለከተ እየተከናወነ የሚገኘውን ህገ ወጥ ቅጥርና ዝውውር በማረም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

ሀገረ ስብከቱና ጠቅላይ ቤተክህነቱ ተናበውና ተግባብተው መስራት በሚገባቸው ጉዳዩች ላይም ሕግንና ሕግን መሰረት አድርገን መስራት ስለሚገባቸው ይህን መድረክ ለማዘጋጀት ተገደናል ያሉት ብፁዕነታቸው የዚህ መድረክ ዓላማ ለመወነጃጀል ለመነቃቀፍና ለመተቻቸት ሳይሆን በመወያየትና በመግባባት በሀገረ ስብከቱ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ነው በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

ጉባኤው በዛሬው እለት በሚያካሒደው ጥልቅ ውይይት ሕግ፣መመሪያ፣ደንቦችና ተቋማዊ አሰራሮችን በጠበቀ መልኩ ሥራዎችን በማከናወን ማዕከላዊነትን ባለማክበር ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ተቋማዊና ሕጋዊ አሰራሮችን በመተግበር በሀገረ ስብከቱና በጠቅላይ ቤተክህነት መካከል መዋቅራዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር የሚያስችሉ ልዩልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotceth.org/a/wp-content/uploads/eotceth-logo2.svg tc2023-11-28 09:59:062023-11-28 09:59:23የጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባዔ አባላት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ የጋራ ጉባዔ በማድረግ ላይ ናቸው።
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተሠራውን የለገዳዲ አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን መረቁ፡፡
  • የወጨ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ሕንጻ በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የተከናወነው የወንዝ ማስቀየስ ሥራ ተጠናቆ በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ተመረቀ።
  • በሸገር ሀገረ ስብከት የታነጸው የደብረ ሣህል ቅዱስ ገብርኤል አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።
  • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሱማሌ ክልል ጅግጅጋ እና የምስራቅ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • December 2025
  • August 2025
  • July 2025
  • June 2025
  • March 2025
  • February 2025
  • January 2025
  • December 2024
  • November 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • July 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • April 2024
  • March 2024
  • February 2024
  • January 2024
  • December 2023
  • November 2023
  • October 2023
  • September 2023
  • August 2023
  • July 2023
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
  • March 2023
  • February 2023
  • January 2023
  • December 2022
  • October 2022
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ እየተካፈሉ ይገኛሉ፤ Link to: ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ እየተካፈሉ ይገኛሉ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በዓለም አብያተ ክርስቲያናት... Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት መሆኑን በመገንዘብ ሕግና መመሪያን አክብሮ እውነትና እውነተኝነትን መርሁ አድርጎ እንዲሰራ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ። Link to: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት መሆኑን በመገንዘብ ሕግና መመሪያን አክብሮ እውነትና እውነተኝነትን መርሁ አድርጎ እንዲሰራ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top